አዳማ
ኣዳማ በአማርኛ ናዝሬት በኦሮሚያ ክልል ለኦሮሚያ በዋና ከተማነት የሚያገለግል የኢትዮጵያ ከተማ ነው። በምስራቅ ሸዋ ዞን በላቲቱድና ሎንጂቱድ 8.55° N 39.27° E ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምዕራብ 100 ኪሎመትር ላይ ይገኛል።
- ናዝሬት ወዲህ ይመራል። ለእስራኤል ከተማ፣ ናዝሬት፣ እስራኤልን ይዩ።
እንደ ሲቲ ፖፑሌሽን መረጃ አዳማ ከተማ የ456,868 ሰዎች መኖሪያ ስትሆን ሲሆን ከኗሪዎቿ 223,560 ወንዶችና 233,308 ሴቶች ናቸው።[1]
አዳማ በትራንስፖርት ማእከልነት የታወቀ ከተማ ነው። ከተማው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ መንገድ ላይ ይገኛል። አዲስ አበባ ጅቡቲና አሰብ (ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት ኢትዮጵያ አሰብን ስትጠቀም) የሚመላለሱ ቁጥራችው ከፍ ያሉ የጭነት መኪኖች የሚያልፉት በአዳማ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚሄደው ምድር ባቡርም አዳማን ያቋርጣል።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.