ናኒ

ናኒ ወይም ናኔሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከኡሩክ ነገሥታት ቀጥሎ የሱመርን ላዕላይነት ለከተማው ለኡር ያዘው። ይህ የኡር 2ኛ ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ንጉሥ ይባላል።

በዝርዝሩ ላይ ለ120 (ወይም እንደ ሌላ ቅጂ ለ54) ዓመታት ነገሠ፤ እነዚህ ቁጥሮች ግን ምንም ታማኝነት የላቸውም። እንደዚያ ረጅም ዘመን እንደ ነበረው አይመስልም። ከናኒ በፊት የነበረው የኡሩክ 2ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንጉሥ አርጋንዴአ ሲባል፣ የአርጋንዴአ ስም ከሌላ ቅርስ ወይም ምንጭ ፈጽሞ አልተገኘምና ምናልባት ላዕላይነቱን ያልገዛ የኡሩክ ከንቲባ ብቻ ይሆናል። መጨረሻው ከሥነ ቅርስ የታወቀው የኡሩክ 2ኛ ሥርወ መንግሥት ንጉስ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ ሲሆን ናኒ ላዕላይነቱን የያዘው ከእርሱ ይመስላል።

የናኒ ስም አለዚያ የሚታወቀው የቱማል ጽሑፍ በተባለው ሰነድ ውስጥ ይጠቀሳል። በዚህ በኩል ናኒ የኒፑር መቅደስ እንደ ጠገነ ሲለን፣ እንግዲህ የሱመርን ላዕላይነት በውነት እንደ ያዘ ይመስላል። ልጁ መስኪአጝ-ናና ተከተለው።

ቀዳሚው
ኡሩክ ንጉሥ
ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ
ሱመር (ኒፑር) አለቃ
2187-2182
ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መስኪአጝ-ናና
ቀዳሚው
ባሉሉ?
ዑር ገዢ
2219-2182
ዓክልበ. ግድም
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.