ነሐሴ ፳፯
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ።
- ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል።[1]
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ።
- ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
ልደት
፲፱፻፲፮ ዓ/ም የኬንያ ሁለተኛው ፕሬዚደንት ዳንኤል አራፕ ሞይ
ዋቢ ምንጮች
- [Studien zur Kulturkunde 104, Köln 1994 p 572; http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/B/ORTBUA05.pdf Archived ጁን 12, 2011 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.