ነሐሴ ፲፩
ነሐሴ ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፩ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፭ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፬ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፰፻፶ ዓ/ም - በብሪታኒያ ንጉዛት እና በአሜሪካ ኅብረት መኻል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የተዘረጋውን አዲሱን የቴሌግራፍ መስመር በመመረቅ ንግሥት ቪክቶሪያ እና የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጄምስ ቡካነን የሰላምታ መልእክት ተለዋወጡ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአገሪቱን የመጀመሪያ አየር-ዠበብ (አውሮፕላን) በዚህ ዕለት ተረከበ። ሁለተኛው አየር-ዠበብ ከጂቡቲ ወደብ እስከ ድሬዳዋ በባቡር ተጭኖ፤ ከድሬ ዳዋ ደግሞ እስከ አዲስ አበባ አሥራ ስምንት የአውሮፓ የፖስታ ቦርሳዎችን ጭኖ እየበረረ ነሐሴ ፴ ቀን ገባ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ዋና መላክተኛ (Ambassador) ዳግላስ ራይት (Douglas A. H. Wright) በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለመስማማት የተዘጋጀውን የውል ረቂቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አስረከበ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከ ፲፰፻፸፯ ዓ/ም ጀምሮ በፈረንሳይ ሥር በቅኝ ግዛትነት ትተዳደር የነበረችው ጋቦን በዚህ ዕለት ነፃ ወጣች። ሊዮን ምባ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ የነበሩት ማዮር ጄነራል ታፈሰ ለማ በደርግ ተይዘው ታሠሩ። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነብሩት አቡነ ቴዎፍሎስ አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በተካተቱ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ቅዋሜ እንዳላቸው አስታወቁ።
- ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ከገዛቸው አሥር ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ በዚህ ዕለት ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገባ ደማቅ አቅባበል ተደርጎለታል።[1]
ዕለተ ሞት
- ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ ልዕልት ፀሐይ በተወለዱ በ፳፫ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
- {{en]] Baldwin, N. C. Abyssinia, 1929-31. An Aero-Philatelic Guide. (Francis J. Field, Ltd.), Sutton Coldfield.
- {{en]] P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- {{en]] THE LONDON GAZETTE ; Issue 36709 published on the 19 September 1944. Page 20 of 26
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.