ነሐሴ ፲
ነሐሴ ፲ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፮ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፭ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን ችሎት እና የዘውድ ምክር ቤት በመሻር ሕገ-ወጥ ከማድረጉም ባሻገር በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ታጣቂ ወታደሮችን እና ታንክ ጭምር በማሠማራት የመሣሪያ ኃይሉን አሳየ። በተያያዘ ሁኔታ ኤርትራውያንን የሚወክሉ የፓርላማ አባላት ሥራቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.