ነሐሴ ፱
ነሐሴ ፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፱ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፯ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፮ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፮ ዓ/ም - የአትላንቲክ ውቅያኖስንና ሰላማዊ ውቅያኖስ ለማገናኘት የተቆፈረው የፓናማ ቦይ ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ጃፓን በቃል ኪዳን አገሮች ተሸንፋ እጇን ስትሰጥ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ሆነ። በዚህ ዕለት ኮሪያም ነጻ ወጣች።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - ለ፫ መቶ ፴፬ ዓመታት በብሪታኒያንጉዛት ሥር በቅኝ ግዛትነት የኖረችው ሕንድ በዚህ ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች። እስላማዊው የሰሜን-ምዕራብ አካልም በዚሁ ዕለት ተገንጥሎ ፓኪስታን በሚል ስም አዲስ አገር ተፈጠረ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.