ኆኅተ አመክንዮ

ኆኅተ አመክንዮ (ሎጅክ ጌትስ) የኤሌክትሪክ ቮልቴጅን በመጠቀም አምክንዮአዊ ስሌትን ለመፈጸም የሚረዱ መሰረታዊ የኮምፒዩተር አካላት ናቸው። ስሌቱን ሲፈጽሙ አንድ ወይም ብዙ የኤሌክትሪክ ቮልቴጆችን እንደግቤት ወስደው በተፈለገው የአመክዮ ህግ መሰረት አንድ ብቻ ውጤት በመሥጠት ነው። በዚህ ተግባር ላይ ከ0-1.5ቮልት እንደ አመክንዮ ውሸት (0) ሲቆጠር፣ ከ3.5-5ቮልት ደግሞ እንደ እውነት (1) ይቆጠራል ማለት ነው።

ዲጂታል ዑደት
ዲጂታል ዑደት · ኆኅተ አመክንዮ · ዕልፍ ኩነት ማሽን

ኆኅተ አመክንዮ፣ የግዴታ ከኤሌክትሪክ ክፍሎች መሰራት የለባቸውም። ነገር ግን ዘመናዊው ኮምፒዩተር ከዚህ ስለሚሰራ በአሁኑ ወቅት ታዋቂነት ያላቸው ኆኅቶች ከኤሌክትሪክ የተሰሩት ስለሆነ ጥናቱም በነዚህ ላይ ያተኩራል። በኤሌክትሪክ ኆኅቶችም ውስጥ ከሚሰሩበት የኤሌክትሪክ ክፍል አይነትእና ባላቸው የአምክንዮ ተግባር መስረት ይከፈላሉ።

የኆኅተ አመክንዮዎች ዓይነቶች ከተግባራቸው አንጻር


This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.