ኅዳር ፳፫
ኅዳር ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፪ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፯፻፺፯ ዓ.ም. ፓሪስ በሚገኘው የእመቤታችን (Notre Dame) ካቴድራል፣ አምባገነኑ ናፖሌዮን ቦናፓርት በፈረንሳይ ከአንድ ሺህ ዓመት በኋላ እራሱን ንጉሠ ነገሥት አድርጎ በማንገሥ ዘውዱን በራሱ ላይ ጫነ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የአሰብ ወደብ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. አቡ ዳቢ፣ አጅማን፣ ሻርጃ፣ ዱባይ እና ኡም አል ቁዌይን በስምምነት የአረብ ኤሚሬት ሕብረትን መሠረቱ።
ልደት
፲፱፻፲፯ ዓ.ም. የቀድሞው አሜሪካዊ ጄኔራል እና በፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን እና በፕሬዚደንት ጄራልድ ፎርድ አስተዳደር የ’ዋይት ሃውስ’ ሥራ አስኪያጅ ፥ በፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን አስተዳደር ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት አሌክሳንደር ሄይግ
፲፱፻፴፱ ዓ.ም. ኢጣልያዊው የፋሽን ሰው ጂያኒ ቨርሳቺ
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.