ኅዳር ፲፩
ኅዳር ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፩ኛው እና የመፀው ወቅት ፵፮ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፬ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - ዩክራይን ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - የብሪታንያ አልጋ ወራሽ ልዕልት ኤልሳቤጥ (የአሁኗ ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ) በለንደን ዌስትሚኒስተር አቤ ሌፍተናንት (አሁን ልዑል የኤዲንበራ ዱከ) ፊሊፕ ማውንትባተን አገባች።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - የልደታን አየር ዠበብ ማረፊያ የተካው አዲሱ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ(የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አውሮፕላን ማረፊያ) በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ። በዚሁ ዕለት ንጉሠ ነገሥቱ የዓመቱን የፓርላማ ጉባዔ ከፈቱ። በዚሁ ዕለት እና ሰዓት የየጠቅላይ ግዛቱ ገዢዎች በተገኙበት ሥርዓት የአስመራ፤ የድሬ ዳዋ እና የጅማ አየር ማረፊያ ጣቢያዎች ተመርቀዋል። [1]
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በአስተዳደር ጥፋት እና በሙስና ወንጀል ተከሰው በልዩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የቀረቡትን የቀድሞ ባለ-ሥልጣናት መመርመሪያ እንዲሆን የተዘጋጀው አዲስ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ አዋጅ ቁጥር ፰ ታውጆ ወጣ። ይህ ድንጋጌ ባ፲፱፻፵፱ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ ተጨማሪ ነው።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ከወላይታ-ሶዶ ተነስቶ በምዕራብ ወለጋ ዞን ወደምትገኘው በጊ መንገደኞችን የጫነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዲ-ሲ ፫ (Douglas C-47A-30-DL) ለመነሳት ሲያኮበክብ ተከስክሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ አደጋ ሦስቱ አብራሪዎቹ ሕይወታቸው አልፏል።
ልደት
- ፲፱፻፲፰ ዓ/ም - በአሜሪካ የ፲፱፻፷፩ ዓ.ም. የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተወዳዳሪ እና የሟቹ የፕሬዚደንት ጆን ፊትዝጄራልድ ኬኔዲ ታናሽ ወንድም ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - ደራሲውና ጋዜጠኛው ጳውሎስ ኞኞ ቁልቢ አካባቢ ተወለደ።
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
- መኮንን (ካፕቴን)፤ "አቪዬሽን በኢትዮጵያ - ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ጥረትና እድገት" (፲፱፻፺፭) ገጽ ፫፻፲
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/178551 Annual Review of 1963
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.