ኅዳር ፲

ኅዳር ፲ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸ኛው እና የመፀው ወቅት ፵፭ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፭ ቀናት ይቀራሉ።


ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞ ባለ-ሥልጣናትን በሙስና እና የአስተዳደር ጉድለት ወንጀል በሕግ ለመመርመር የተሠየሙትን ሁለት ልዩ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ሕጋዊ የሚያደርገው አዋጅ ቁጥር ፯ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ይፋ ተደረገ።
  • ፲፱፻፸ ዓ/ም - የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳትእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ምናኽም ቤጊን ግብዣ በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ “ክኔሰት” ንግግር አደርጉ። ሳዳትም ይኼን ታሪካዊ ድርጊት በመፈጸም የመጀመሪያው አረባዊ መሪ ናቸው።

ልደት

  • ፲፱፻፲ ዓ/ም - አገሯን በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ ያገለገለችው ኢንዲራ ጋንዲ አላሀባድ በሚባል ሥፍራ ተወለደች።

ዕለተ ሞት



ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974




የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.