ቼኪንግ አካውንት
ቼኪንግ አካውንት ማለት ባንኮች እና መሰል ተቋማት ገንዘብን ጥሩ ዋስትና ባለው ስፍራ ለማስቀመጥና፣ ያ ገንዘብ በተፈለገ ቁጥር በቀላሉ ለማውጣት እንዲያስችል ብለው የፈጠሩት የፋይናንሻል አግልግሎት አይነት ነው።
የቼኪንግ አካውንት ግልጋሎትን ለመጠቀም አካውንት ቁጥር ያስፈልጋል። አካውንት ቁጥሩ የተለያዩ ሰወችንና ተቋማትን ገንዘብ ለያይቶ ለማስቀመጥ ይረዳል። አንድ ሰው መታወቂያውን ሌሎች መለያ ፋይሎቹን በመጠቀም የቼኪንግ አካውንት ከከፍተ በኋላ፣ ባንኩ ለግልሰቡ የቼክ ቡክ ይሰጠዋል። ቼክቡክ ከሁለት ነገሮች ይሰራል፣ እነርሱም ቼክና ዲፖዚት ስሊፕ ሲሆኑ፣ ቼኮች ከአካውንት ቁጥር ውስጥ ባለ ገንዘብ መሰረት የትም ቦታ ለመክፈል ሲያገለግሉ፣ ዲፖዚት ስሊፕ ባንክ ቤት ሄዶ ወደ ተከፈተው ቼኪንግ አካውንት ቁጥር ገንዘብ ለመክፈል (ለማስቀመጥ) ይረዳል።
እያንዳንዱ ቼክ ቡክ እና ዲፖዚት ስሊፕ፣ ራውቲንግ ቁጥር እና አካውንት ቁጥር ይኖረዋል። ራውቲንግ ቁጥሩ፣ ባንክ ቤቱን ለይቶ ለማወቅ ሲረዳ፣ አካውንት ነምበሩ ደግሞ የደምበኛውን ማንነት ይለያል።
ዳይሬክት ( ቀጥተኛ) ዲፖዚት
ዳርይሬክት ዲፖዚት፣ አንድ ሰራተኛ፣ የሳምንት ወይንም የወር ደመዎዙ ፣ ከቀጣሪው ድርጅት ቀጥታ ወደ አካውንት ቁጥሩ ሲተላለፍ ነው። ይህ እንግዲህ ሰራተኛው የተከፈለውን ደመዎዝ በየሳምንቱ/ወሩ ከመስሪያ ቤት ወደ ባንክ በማመላለስ ጊዜ እንዳያጠፋ ይረዳዋል። በተጨማሪም፣ በቋሚ ሁኔታ ገንዘቡ ስለሚተላለፍ አንድ አንድ ወጭወችን ያለ ምንም ውጣውረድ ለመክፈል ይጠቅማል።