ትሂድ ትመልሰው

መቅዴላ አፋፉ ላይጩኸት በረከተ ፣ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ ፡፡ የቅኔው አይነት የኀዘን ቅኔ ሲሆን አፈታቱ ታሪክን በማወቅ ይሆናል ፡፡ ሕብረ ቃሉ- ወንድ አንድ ሰው የሚለው ነው ፡፡ ታሪኩ መቅዴላ ታላቅ ስራ የሰራው አጼ -ቴዎድሮስ ነው !! ሠሙ፡-መቅዴላ አፋፍ ከፍተኛ ለቅሶና ጩኸ አለ የሞተው ወንድ በቁጥር አንድ ሲሆን ምንያህል ሴት እነዴሞተ አልታወቀም የሚል ነው ፡፡ ወርቁ፡- ጀግናው አጼ-ቴዎድሮስ ሞተ የሚል ነው ፡፡

ሊበላ ብሎ አንበጣ ፣ ራዛው በላይ መጣ ፡፡ ሕብረ ቃሉ- ራዛው በላይ መጣ ሠሙ፡- አንበጣው አዝመራውን ሊበላ ሲል ራዛ የተባለው አሞራ በሰመይ መጣበት የሚል ነው ፡፡ ወርቁ፡- ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት እወራለሁ ሲል ጀግናው በላይ ዘለቀ ለቃቅሞ ጨረሰው ማለት ነው ፡፡ የቅኔው አፈታት ስልት ታሪክን በማወቅና ነገሮችን በማመሳሰል የመፍታት ስልት ነው ፡፡ ራዛ ማለት ትልቅና ፈጣን አሞራ ነው ለዚህም ነው ጀግናውና ወደርየለሹ በለይ ዘለቀ በፍጥነቱና ቅልጥፍናው በራዛ የተመሠለው ፡፡

አጼ-ዮሃንስ ይዋሻሉ ፣ መጠጥ አልጠጣም እያሉ ፣ ሲጠጡ አይተናል በእርግጥ ፣ ራስ እሚያዞር መጠጥ ፡፡


የአፈታት ስልቱ ታሪክን በማወቅ ነው ፡፡ ሕብረ -ቃል -ራስ እሚያዞር መጠጥ ሠሙ -ንጉሱ አጼ-ዮሃንስ መጠጥ አልጠጣም ብለው ይዋሻሉ(ውሸት ያወራሉ)ነገር ግን ተደብቀው ሲጠጡ ታይተዋል ማለት ነው ፡፡ ወርቁ፡-1) ንጉሡ ዮሃንስ ከሱዳኖች ሲዋጉ አንገታቸዉ ተቆረጦ በሱዳኖች ተወሰደ ማለትም ሱዳን ድረስ ጭንቅላታቸው ተነከራተተ (ዞረ) ማለት ነው፡፡ ቃላትን አጥብቆና አላልቶ በማንበብ የመፍታት ዘዴ

ቻይና ማበር ገባች ያባቱዋም ልነበር ፣ እነሱን መጋበዝ ቡን አድርጎ ነበር ፡፡

ሕብረ -ቃል -ቡን አድርጎ ነበር አፈታቱ ቃሉን አጥብቀንና አላልተን ስናነበው በሚያመጣው የትርጉም ለውጥ ነው ፡፡ ሠሙ -ቻይናወችን መጋበዝ ቡና አፍልቶ ነበር ብሎ መቆጨቱን ይገልጻል ፡፡ ወርቁ- ቻይናዎች በተለያየ ምክንያት ወደ ሀገራችን ገቡ ቡን (አመድ) አድርገን ነበር ማጥፋት የሚል የቁጭት ስሜት ይገልጻል ፡፡

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.