ታኅሣሥ ፪
ታኅሣሥ ፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፪ተኛው እና የወርኅ መፀው፷፯ተኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፫ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ መንግሥት ኢትዮጵያ አገራችንን በግፍ ከወረረች በኋላ የተሰነዘረባትን ነቀፋ እና የንግድ እገዳ ምክንያት በማድረግ ከየዓለም መንግሥታት ማኅበር አባልነት ወጣች።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ሕጻናት ዕርዳታ ድርጅት (UNICEF] ተመሠረተ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - የአንበሳ አውቶቡስ ህጋዊ ሰውነት በማግኘት በአክሲዮን ከተቋቋመ በኋላ አረንጓዴና ቢጫ የተቀቡ ፲ አውቶቡሶችን ይዞ ሥራ ጀመረ፤ እነዚህም አውቶቡሶች በከተማዋ አራት መስመሮች ላይ ብቻ የተሰማሩ ነበሩ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ታዋቂው አርጀንቲናዊ የአብዮት መሪ ቼ ጉቬራ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርግ ያልታወቀ ሽብርተኛ ከውጭ በሕንጻው ላይ የሞርታር ጥይት ተኮሰ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት የፔሩውን ተወላጅ ሃቪዬር ፔሬዝ ደ ኩዌያርን የድርጅቱ አምስተኛ ዋና ጸሐፊ እንዲሆኑ መረጣቸው።
ልደት
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የሩሲያው ተወላጅና የሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ሶልዤኒትሲን በዛሬው ዕለት በኪስሎቮድስክ ተወለደ። ሶልዤኒትሲን በስታሊን ዘመን አድሀሪ በመባል ተወንጅሎ በሳይቤሪያ ግዛት ውስጥ በእሥራትና በግዞት በነበረበት ወቅት የጻፈው “የጉላግ አርቺፒላጎ” በተባለው ድርሰቱ በዓለም ታዋቂነትን ያተረፈ ጸሐፊ ነበር።
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081211.html
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/December_11
- አውራምባ ታይምስ፤ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.