የቲኩናኒ ፕሪዝም

የቲኩናኒ ፕሪዝምሶርያ የተገኘ በአካድኛ የተጻፈ የሸክላ ቅርስ ሲሆን የጥንቱ ከተማ የቲኩናኒ ንጉሥ የቱኒፕ-ተሹፕ 438 «ሃቢሩ» ወታደር ቅጥረኞች ስሞች ይዘርዝራል። ከነዚህ ስሞች አብዛኞቹ የሑርኛ ስሞች ሲሆኑ የተረፉት ሰማዊ ቋንቋ ስሞች ናቸው። አንድ ስም ብቻ ካሥኛ ይመስላል። ከዚህ የተነሣ ብዙ ሃቢሩ ከሑራውያን ብሔር እንደ መጡ ታስቧል። ይህ ንጉሥ በኬጥያውያን መንግሥት ንጉስ 1 ሐቱሺሊ ዘመን ወይም 1550 ዓክልበ. ገደማ እንደ ገዛ ይታወቃል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.