ብሳና

ብሳና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ዛፉ ባብዛኛው ከ7 እስከ 15 ሜትር ይደርሳል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

በኢትዮጵያ በጣም ተራ ነው።

የተክሉ ጥቅም

ፍሬዎቹና የሥሮቹ መረቅ ለአባለዘር በሽቶች ተጠቅመዋል።

የተደቀቀው ልጥ ከኮሶ ወይም መተሬ ጋር ተቅላቅሎ ትልን ያስወጣል።

ዘሮቹና ሙጫዎቹ መርዛም ናቸው፣ ለአሣ መርዝ ይጠቀማሉ።

የቅጠሎቹ ውጥ ለአናት እከክ ይጠቀማል።

ወፍ በሽታ፦ የብሳና ቡቃያ ቅጠል መረቅ ከሰንሰል ጋር ተቀላቅሎ፣ ቁንዶ በርበሬና ቅቤ ይጨምር ለ፫ ቀን በዳቦ ይበላል፤ በርካታ ወተትም ይጠጣል እንጂ ሥጋ ወይም ዘይታም ምግቦች መተው አለበት።[1]

ከልዩ ልዩ ቦታዎች ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ፣ የብሳና ላፒስ እንደ ቅባት ለችፌቋቁቻ ወይም ጭርት ያከማል። እንዲሁም የብሳና ዛፍ ልጥ ዱቄት ለቁስሎች ይለጠፋል። የአገዳው ልጥ ዱቄት በወተት ለልብ ድካም ይጠጣል።[2]

የብሳና፣ የጨጎጊትና የክትክታ ቅጠላቅጠል ተደቅቀው እንደ ለጥፍ ደግሞ ለቁስል ይለጠፋል።

ትኩሳት («ምች»)፣ የብሳና ቅጠልና የቀበሪቾ ሥር እንደ ጢስ ይናፈሳል። የብሳና ቅጠል ከተለያዩ ሌሎች አይነት ቅጠሎች ጋር በውሃ ተፈልቶ እንፋሎቱ ለ«ምች» ይናፈሳል፦ ለምሳሌ ነጭ ባሕር ዛፍዳማ ከሴዋንዛጥንጁት ቅጠል፣ ፌጦ ዘር።

ውሻ በሽታ፦ የብሳና ልጥ፣ የእምቧይየገበር እምቧይና የግንዶሽ ሥር፣ የጽድ ቅጠልና የጤፍ ዘር፣ አንድላይ ተጋግሮ ተድቅቆ በውሃ ይጠጣ። እንዲሁም ለእንስሳ ውሻ በሽታ፣ በትንሽ ጤፍ እንጀራ ይበላ።[3]

ዘጌ ልሳነ ምድር ጥናት እንደ ተዘገበ፣ ለቁርባ ማከም የብሳና ቅጠል ወደ ወጥ ይጨመራል። የቅጠሉም ዱቄት ለተቅማጥ ይጠጣል፣ ለወፍ በሽታ ደግሞ ለ፯ ቀን ይጠጣል።[4]

የውጭ መያያዣ


  1. አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
  3. በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  4. የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.