ቡር-ሲን

ቡር-ሲንሱመርኢሲን ሥርወ መንግሥት 7ኛው ንጉሥ ነበረ (1806-1785 ዓክልበ. የነገሠ)። የኡር-ኒኑርታ ልጅና ተከታይ ነበረ።

ከኢሲን በላይ በኒፑር ስለ ገዛ «የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ተባለ። ቅርሶቹ እንደሚያመልክቱ ምናልባት ከ1788 እስከ 1785 ድረስ ኡርን ከላርሳ ያዘ። እንዲሁም በዚያው ወቅት ቡር-ሲን «የኪሱራ ንጉሥ» ተደረገ። በዘመኑ ሌሎች ተወዳዳሪዎች መንግሥታት ደግሞ በባቢሎንካዛሉ-ማራድኢሊፕ-አኩሱምኤሽኑናኡሩክአሹር ተገኙ።

ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ፳፩ ወይም ፳፪ ዓመታት እንደ ነገሠ ሲለን፣ ከዘመኑ ፱ የዓመት ስሞች ብቻ ይታወቃሉ።[1] ከመጀመርያው ፪ ዓመቶቹ በቀር የሌሎቹ ዓመታት (a-g) ቅድም-ተከተላቸው እርግጥኛ አይደለም።

ቀዳሚው
ኡር-ኒኑርታ
ኢሲን ንጉሥ
1806-1785 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሊፒት-ኤንሊል
ቀዳሚው
ዚክሩም
ኪሱራ ንጉሥ
1788-1785 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኢቢ-ሻማሽ

ዋቢ ምንጮች

  1. የቡር-ሲን ዓመት ስሞች
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.