ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ

ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በኢንጂ. ሃይሉ ሻውል የሚመራ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረ ፓርቲ ነበር። ይህ ፓርቲ በግንቦት 7 ቀን 1997 በተካሄደው ምርጫ ተመሳሳይ አቋም ያላቸውን መኢአድኢዴአፓ-ማድህንኤዴሊንና ለዚሁ አላማ የተመሰረተውን ቀስተ ደመናን የሚያካትት ስብስብ ሆኖ የተመሰረተ ነበር። በ1997 ኣ.ም በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ቅንጅት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት (በአንዳንድ ውገኖችም አሸንፎ እንደነበር) ይታወቃል። የአዲስ አበባን አስተዳደር ማሸነፉም በተቀናቃኙ ፓርቲ በኢህአዴግ የታመነ ነበር።

ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ የነበረው መንግስትባልተረጋገጠ ሁኔታ በምርጫ በማሰነፉና ከምርጫ በኋላ የተደረጉት ድርድሮች ዘልቀው ባለመሄዳችው ከፍተኛ አለመረጋጋት ተፈጥሮ ቆይቶ መንግስት የቅንጅት መሪዎችን እንዲሁም ተቃውሞ ያስሙትን ብዙ ወገኖችን በተለያዩ ክሶች ወንጅሎ በእስራት ይዞ ነበር። ሆኖም ጥቂት የቅንጅት አባሎች የፓርላማ ወንበራችውንም ተረክበው በመንቀሳቀስ ላይ ነበሩ።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.