ቅኔ
ቅኔ ማለት፡ 'ቀነየ' ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ አመሰገነ (ምስጋና) ማለት ነው። ወይም፡ 'ቀነየ' ፡ገዛ፡ የሚለውን፡ አንቀጽ፡ ያስገኘ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ፍችውም፡ 'መገዛት'፡ ማለት፡ ነው። 'ቁሙ፡ እንከ፡ ወኢትሑሩ፡ ዳግመ፡ ውስተ፡ አርዑተ፡ ቅኔ'፡ እንዲል፡ (ገላ.፥5፥1)፥ ቅኔ፡ ማለት፡ መገዛት፡ ማለት፡ ከኾነ፥ ይህ፡ ከያንዳንዱ፡ ሰው፡ በየጊዜው፡ የሚመነጨው፡ እንግዳ፡ ድርሰት፡ ስለ፡ ምን፡ ቅኔ፡ ተባለ፡ ቢሉ፥ ፍጡር፡ ዐዲስ፡ ዐዲስ፡ ምስጋና፡ እየደረሰ፡ በማቅረብ፥ ለፈጣሪው፡ መገዛቱን፡ የሚገልጥበት፡ ስለ፡ ኾነ፡ ነው። ለፍጡራን፡ የሚደረሰውም፡ ቅኔ፥ ቅኔው፡ የሚደረስለት፡ ፍጡር፡ ከቅኔ፡ ደራሲው፡ በላይ፡ ክብር፡ ያለው፡ መኾኑን፡ የሚገልጽ ፡ ድርሰት፡ ስለ፡ ኾነ፥ መገዛትን፡ ከማመልከት፡ የራቀ፡ አይደለም።
አንድም፥ ሕዋሳተ፡ አፍኣን፣ ሕዋሳተ፡ ውስጥን፡ ለኅሊና፡ አስገዝቶ፥ በተወሰነ፡ ቍርጥ፡ ሐሳብ ፡ የሚታሰብ፡ ስለ፡ ኾነ፥ ቅኔ፡ ተብሏል። ይኸውም፡ ሊታወቅ፥ በቅኔ፡ ምስጢር፡ ልቡ፡ የተነካ፡ ሰው፥ ቅኔ፡ በሚያስብበት፡ ጊዜ፥ እፊቱ፡ የሚደረገውን፡ ነገር፡ እያየ፣ እየሰማ፥ አይሰማም። ከዚህም፡ የተነሣ፥ በጎንደሮች፡ መንግሥት፥ የቍስቋሙ፡ አለቃ፡ በእልፍኙ፡ ውስጥ፡ ምንጣፉን፡ አስነጥፎ፥ መጻሕፍቱን፡ እፊቱ፡ ደርድሮ፥ ለበዓለ፡ ቍስቋም፡ የሚቀኘውን፡ ቅኔ፡ ሲያወጣና፡ ሲያወርድ፥ ንጉሡ፡ ዘው፡ ብለው፡ ቢገቡ፥ ልቡ፡ ተመሥጦ፥ ሊያያቸው፡ ባለመቻሉ፥ ቀና፡ ብሎ፡ ሳያያቸው ፡ ቁጭ፡ እንዳለ፡ ቀረ። ንጉሡም፥ ነገሩ፡ ደንቋቸው፥ ፍጻሜውን፡ ለማየት፥ ርሱን፡ ዐልፈው፡ ዐልጋ፡ ላይ፡ ተቀምጠው፥ ኹኔታውን፡ ይመለከቱ፡ ዠመር።
ብዙ፡ ሰዓት፡ ካሳለፈ፡ በዃላ፥ አእምሮው፡ ሲመለስ፥ ንጉሡ፡ ተቀምጠው፡ ቢያይ፥ ደንግጦ፡ ተነሥቶ፡ እጅ፡ ነሣ። ንጉሡም፦ ምነው፧ ምን፡ ኾነኽ፡ነው፧ ቢሉት፦ ጃንሆይ፥ ቍስቋምን፡ ያኽል፡ ደብር ፡ አምነው፡ ሾመውኛል፤ ለበዓል፡ የተሰበሰበው፡ ሰው፡ አለቃው፡ ምን፡ ይናገር፡ ይኾን፧ እያለ፡ ዐይን፡ ዐይኔን፡ ሲያየኝ፥ ያልኾነ፡ ነገር፡ ቢሰማ፡ ደብሩን፡ አዋርዳለኹ፥ ጃንሆይንም፡ አሳማለኹ፥ እኔም፡ አፍራለኹ፡ ብዬ፥ ቅኔ፡ እቈጥር፡ ነበር፡ አለ፡ ይባላል።
አንድም፥ ቅኔ፡ ማለት፥ 'ተቀንየ'፡ ሙሾ፡ አወጣ፥ ግጥም፡ ገጠመ፥ አራቆ፡ ተናገረ፥ አዜመ፥ አንጐራጐረ፥ መራ፥ ዘፈነ፡ ካለው፡ የወጣ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ስለዚህ፥ ቅኔ፡ ማለት፥ ባጪሩ፥ ጠቅላላ፡ ትርጕሙ፥ ሰው፡ ከራሱ፡ አንቅቶ፡ ለእግዚአብሔር፡ ዐዲስ፡ ምስጋና፡ ላቅርብ፡ ባለ፡ ጊዜ፥ ምሳሌ መስሎ፥ ምስጢር፡ አሻሽሎ፡ ግጥም፡ በመግጠም፥ የልቦናውን፡ ዕውቀት፣ የአእምሮውን፡ ርቀት፡ የሚገልጽበት፥ የዕውቀቱን፡ ደረጃ፡ የሚያስታውቅበት፥ የሰሚንም፡ ልቡና፡ የሚያነቃቃበትና፡ የሚያራቅቅበት፡ ድርሰት፡ ማለት፡ ነው። ከዚህም፡ የተነሣ፥ መጋቢ፡ መርሻ፡ ኀይሉ፡ የተባሉ ፡ የዲማው፡ ባለ፡ ቅኔ፦ የሰውን፡ ዕውቀቱን፡ መጠን፡ የማውቀው፡ በቅኔው፡ ነው፡ ይሉ፡ ነበር፡ ይባላል።
ከስም ውስጥ ይተሽሞነምነ ወርቅ እንደሚወጣ ሁሉ ከቃላትም የተደበቀ ምስጢር ሲወጣ ያ ጥበብ ሰምና ወርቅ (ቅኔ) ይሰኛል።
የአማርኛ ቅኔወች
- ትሂድ ትመልሰው
- ከጥላቸው እራቅ
- ያህል ነው እንጂ
- መፍቻ መንገዶች
የግዕዝ ቅኔወች
ንሁር በፍናዌሀሙ ወንትሉ በኣሰሮሙ
ህፃናት አእባን ኢትሁሩ ከዊነ እክሙ ሠላሳ ዉስተ ቤተ ዮሤፍ ባእድ አምጣነ ሀሎ አንበሣ ኒቆዲሞስ ገብር በሌሊተ ግርማ ቀጥቅጦ ለአስተብርኮ ብርክ ጸርከ እስከ ይወጽዕዘሂጦ