ቁርአን

ቅዱስ ቁርአን ወይንም ቁርአን) የመሃከለኛዉ አለም የእስልምናቅዱስ መጽሃፍ ወይም የእምነት ጽሁፍ ነዉ፣ በዚህም ትምህርት ይህ ጽሁፍ የመጣዉ በአላህ ፈቃድ ቃሉን በጂብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሀመድ የወረደ የአላህ ቃል ነው። ቅዱስ ቁርአን ለመጀመርያ ጊዜ በአረብኛ ነበር የተጻፈዉ። አላህ ለቁራን ቃል ገብቶለታል እሱም ማንም ሰዉ መበረዝ እንደማይችል እና ማንም ሰዉ ቃሉን ቀይሮ ህጉን ሊአሳስት እንደማይችል ነዉ። አላህ ሁልጊዜም ከመበረዝ የሚጠብቀዉ በአለም ላይ ያለ ብቸኛው መጽሃፍ ነዉ። ይኅም በአማርኛ የተተረጎመ ቁርዓን ነዉ።

የተዋበ የአረብኛዉ ቁርአን ሽፋን

ቁርአን ሰዎች እና አጋንንት እንኳ ቢሰበሰቡ የሱን ተመሳሳይ አንቀጽ ወይም አረፍተ ነገር ማምጣት ይችሉ እንደሆነ ይሞክሩ በማለት ተአምረኛነቱን እና እውነተኛነቱን አረጋግጧል። ቁርአን ከመበዘረዝ እና ከመከለስ የጠራ ነው። እንደዚህም የሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እንደሆነ ሳይበረዝ እና ሳይከለስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቆያል፤ ምክንያቱም አላህ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል ስለገባለት ቁርአንን በተመለከተ ሙስሊሞች'

  1. ' ምንም አይነት ልዩነት የለባቸውም። በአረብኛ ተጽፎ አንድ ቃል ይቅርና አንድ ፊደል እንኳ ሊጨመር ቢችል ወይም ቢቀነስ በቀጥታ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል።

የሰው ልጆች በዚህ ምድርም ይሁን በመጭው አለም ሰiላም እና እርጋታ ከፈለጉ ሙስሊም ሆነው በቁርአን መመራት አለባቸው የሚል ትምህርት ያቀርባል።

የውጭ መያያይዣ

:
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.