ቀይ ዋቅላሚዎች

ቀይ ዋቅላሚዎች ወይም ሮዶፋይታ ቀደምት ከሆኑት ውን ኑክለሳውያንዋቅላሚ ቡድኖች አንዱ ነው።[1] ሮዶፋይታ በአሁኑ ጊዜ ከታላላቅ የዋቅላሚ ክፍለስፍኖች አንዱን በማቀፍ የስር አተ ምደባ ክለሳ እየተደረገላቸው ያሉ ከ7,000 የሚበልጡ የታወቁ ዝርያዎችን በስሩ ይይዛል። [2]

Chondrus crispus
ቀይ ዋቅላሚ

አብዛኛዎቹ ዝርያዎች (6,793) በፍሎሪዴዎፋይሲዬ ( መደብ ) ውስጥ ይገኛሉ፤እናም በአብዛኛው በርካታ ታዋቂ የባህር አረሞችን ጨምሮ ባለብዙ ህዋስ የባህርውሰጥ ዋቅላሚዎችን, ያካትታል። [2] [3]

ቀይ ዋቅላሚዎች በባህር ውስጥ በብዛት ይገኛሉ ነገር ግን በአንጻራዊነት በለጋ ውሃማ አካላት ውስጥ በጣም አናሳ ናቸው። [4] በግምት 5% የሚሆኑት የቀይ ዋቅላሚ ዝርያዎች በለጋ ውሃማ አከባቢዎች ውስጥ የሚከሰቱ ሲሆን አባኛዎቹ የሚገኙት በሞቃታማ አካባቢዎች ነው።. [5]

ኢጾታዊ መደብ በሆነው ሲያኒዶፋይሲዬ ውስጥ የሚገኙ እና በባህር ዳርቻ ዋሻ ከሚኖሩ ሁለት ዝርያዎች በስተቀር የየብስ ዝርያዎች የሉም። ምናልባትም ይህ የሆነው የመጨረሻው የጋራ ቀዳሚ ዝርያ በዝግመታዊ ለውጥ ማነቆ ምክኒያት የዝግመታዊ ለውጥ ተጣጣፊነቱን እና ከማዕከላዊ ዘረመሉ ወደ25% የሚሆነውን በማጣቱ ሳይሆን አልቀረም። [6] [7]

ዋቢ ምንጮች

  1. Lee, R.E. (2008). Phycology (4th ed.). Cambridge University Press. ISBN 978-0-521-63883-8.
  2. "Algaebase" (2016).
  3. D. Thomas. Seaweeds.
  4. Dodds, Walter K. (Walter Kennedy), 1958- (7 May 2019). Freshwater ecology : concepts and environmental applications of limnology. https://www.worldcat.org/oclc/1096190142.
  5. Sheath, Robert G.. The biology of freshwater red algae.
  6. Why don't we live on a red planet?
  7. Azua-Bustos, A; González-Silva, C. Extreme environments as potential drivers of convergent evolution by exaptation: the Atacama Desert Coastal Range case.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.