ቀራንዮ መድኅኔ ዓለም

ደብረ ቀራንዮ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ደብሩ ለመጀመርያ ጊዜ የተመሠረተው በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ1826 ዓም ሲሆን ከአዲስ አበባ ቤተክርስቲያኖች በዕድሜ ትልቁ ነው። አሁን ያለውን ቤተክርስቲያን ያሠሩት ደግሞ አፄ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው።የደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ዳግማዊ ቀራንዮ ዘኢትዮጵያ

ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አንዱና ቀዳሚው የሆነው ይህ ደብር የተመሰረተው በ1826 ዓ/ም በንጉስ ሳህለስላሴ ሲሆነ አመሰራረቱም ንጉስ ሳህለ ስላሴ በሸዋ ግዛታቸው ውስጥ እየተዘዋወሩ አንድነትን ለማስተማር ባላቸው ጽኑ ዓላማ መሰረት ሰራዊታቸውን አስከትለው 1826 ዓ/ም ወደ ደቡብ ተጒዋዙ በዚህ ጉዙአቸው በወሊሶ በኩል አልፈው የጉራጌን ህዝብ ሀገር አስተማሩ ጉዞአቸውንም በማራዘም በአርሲ አካባቢ የሰሜኑን ክልል እነዲማር አድርገው በግራኝ ምክንያት ተለያይቶ የነበረውን ህዝብና ክልል አንድ ካደረጉ በኋላ ከጉዞአቸው ሲመለሱ ዛሬ ቀራንዮ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያነ ከተመሰረተበት ቦታ ደርሰው ጥቂት ዕረፍት ቆይታ አደረጉ፡፡
በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ አመልክቷቸው በዚህ ቦታ እግዚአብሔር እንዲመለክበት በቦታውም ፅላተ መድኃኔዓለም ከእቲሳ መጥቶ በመረጡበት ቦታ እንዲተከል ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ ታቦቱ በንጉሱ ትዕዛዝ መጥቶ በመረጡት በተዘጋጀለት መቃኞ ውስጥ ቢያርፍም ቦታው ደን ለበስ ስለነበረና ብዙ ኢአማንያን እንዲሁም ሽፍቶች ስለነበሩ መቃኞ ከአንድም ሶስት ጊዜ ሊቃጠል ችሎአል ሆኖም የንጉሱ አላማ ዕውቀትን ማበልጸግ ቤተክርስትያንን ማነጽ ስለነበር የሽፍቶቹን ኃይል በእግዚአብሔር አጋዥነት አሸንፈዋቸዋል ቤተክርስትያኑንም አጠገቡ ከሚገኘው አቃቂ ወንዝ ጋር በማጣመር አቃቂ መድኃዓለም ተብሎ ይጠራም ነበር የመድኃነኔዓለም ጽላት አመጣጥ በሚወሳበት ወቅት መምህር ተክለወልድና አባ ደጀን ተጠቃሽ ናቸው መምህር ተክለወልድ ከእቲሳ አምጥተው በዚህ ቦታበተሰራውመቃኞ ውስጥ እንዳስቀመጡት በአገልግሎታቸውም ወቅት ከባድ ፈተና እንዳጋጠማቸው ይነገራል በሌላ በኩል ደግሞ በሁለተኝነነት የጠቀስናቸው አባደጀን እንዳመጡት ይነገራል፡፡
ከንጉስ ሳህለ ስላሴ ትዕዛዝ ተቀብለው ጽላቱም ከእቲሳ አስይዘውየላኳቸው አባ ዘወልደማርያም የተባሉ አባት እንደነበሩ ይታወሳል አባ ዘወልደማርያም በዚህም ቦታ ቦታ ሀገር በቀል እጽዋትን ተክለዋል አባ ደጀንም ከጽላቱ ጋር ድርሳነ ማህየዊ የተባለ በዚህቤተክርስትያን ብቻ የሚገኝ መጽሀፍ አምጥተዋል ደብሩ በዚህ አይነት ሁኔታ ከቀጠለ በኋላ 1899 ዓ/ም አጼ ምንሊክ ባወጁት አዋጅ የአብያተ ክርስትያናያ ምስረታና ዕደሳ መሰረት ቤተክርስትያኑ በሶስት አመት ውስጥ ተጠናቆ 1901 አጼው ባሰሩት አዲስ የሳር ክዳን ትልቅ ቤተክርስትያን ውስጥ ሊገባ ችሏል አጼ ምንሊክም በዚያው ዓመት በጃን ሜዳ መኳንንቱንና መሳፍንቱ ህዝቡ በተሰበሰበበት አቃቂ መድኃኔዓለም እንዳይባል እንዲህም ብሎ የጠራ ይቀጣል ከአሁን በኋላ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ይባል እንጅ ብለው በአዋጅ ተናግረው አጸደቁ ቀራንዮ የሚለው ስያሜ ምንም እንኳን ለቤተመቅደሱ የተሰጠው ስያሜ ቢሆንም ለክልሉ ለአካባቢው እስከ አሁን ድረስ መጠሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡
አፄ ምንሊክም ጌታችን ከተሰቀለበት ከኢየሩሳሌም ቀራንዮ አፈር በማስመጣት በግቢው ውስጥ ካስፈሰሱ ብኋላ ዳግማዊ ቀራንዮ ብለው መሰየማቸውን ታሪክ ይናገራል አዲሱን የሳር ክዳን ቤተክርስትያን ከንጉሱ ትዕዛዝ ተቀብለው ከነሰራተኞቻቸው ያሰሩት ኋላም የደብሩ የመጀመሪያ ገበዝ በመሆን ደብሩም ለብዙ አመታት የመሩት ደጃዝማች ወልደገብርኤል ነበሩ ደጃዝማች ወልደገብርኤል የቤተመንግሰቱንና የቤተክርስትያኑን ስራ በትጋት በመስራት ለቤተክርስትያኑ ታላቅ ሰው ነበሩ ኋላም ደጃዝማች ወልደገብርኤል የቤተመንግስቱ ስራ ፋታስላልሰጣቸው የደብሩን ቅርስና ሀብት ለህይወታቸው ሳይሳሱ ለጠበቁት ለቄሰገበዝ አስራት ሀብተሚካኤል አስረከቧቸው 1901 የተሰራው አዲሱ ቤተመቅደስ የምዕመናን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛበ መምጣቱ የተነሳና ለአገልግሎት አይመችም ነበር ይህንንም የተመለከቱት ንግስት ዘውዲቱ ሌላ ዘመናዊና ሰፊ ቤተክርስትያን ለማሰራት ያቅዳሉ ነገር ግን ሀሳባቸውን እውን ሳያደርጉ 1922 ዓ/ም ያርፋሉ ፡፡

ከዚህም በኋላ 1922 በዚያው ዓመት በግርማዊ ጃንሆይ እንደነገሱ የንግስት ዘውዲቱ ዕቅድና አላማ የነበረውና ታላቁን ቤተመቅደስ አሰሩ የቤተመቅደሱም ስራ 1922 ተጃምሮ 1925 በግርማዊ ጃንሆይ በነገሱ በሶስተኛ ዘመነ መንግስታቸው ተጠናቀቀ በዚሁ ዓመትም በታላቅ ድምቀት በአዲሱ ቤተክርስትያን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ አሁን የሚገኘው ቤተክርስትያነ ግንባታው ተሰርቶ እስኪያልቅ ድረስ ደጃዝማች ወልደገብርኤል ለአፅማቸው ማረፊያ ባሰሩት ባለአንድ ፎቅ የቆርቆሮ ክዳን ቤት ውስጥ ነበር በዚህም ፅላቱ ሳለ ቅዳሴው በፎቁ ማህሌቱ በታች ይስተናገድ ነበር፡፡

አሁን የሚገኘው ህንጻ ቤተክርስትያን ምን ያህል ገንዘብ እንደፈጀ የሚገልጽ ሰነድ የለም ነገር ግን በግርማዊ ጃንሆይ በግል ገንዘባቸው እንዳሰሩት ታሪክ ይናገራል ህንጻውን የሰሩት ሁለት የጣልያን ዜግነት የነበራቸው በዚያም ዘመን በህንጻ ስራ ታዋቂ በነበሩት ሙሴ ፓፓጀማና ኩኞስ ነበሩ በደብሩም ብዙ የተለያዩ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን በአሁኑም ሰዓት ከ350 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ እጽዋት ሲገኙ ከዚህም በተጨማሪም ደብሩ ከተለያዩ ነገስታት የተሰጡትና በአንዳንድ አባቶች የተሰጡት ጥንታዊ የብርሃና መጽሃፍት አልባሳት የተለያዩ ውድ የወርቅ የብር የነሀስ መስቀሎች ጥላዎች በንግስት ቪክቶርያ ለሳህለ ስላሴ የተሰጡ የተለያዩ ውድ ስጦታዎችና የባላብዙ ታሪከና ቅርስ ባለቤት ደብር ነው ደብረ ቀራንዮ በአጥቢያው ለሚገኙ ደብራትና አብያተክርስትያናት ብሎም ለአዲስ አበባ ከተማ መመስረት መነሻም ነው፡፡
http://anketsetewahdo.blogspot.com/

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.