ሹ-ኢሊሹ

ሹ-ኢሊሹ ከ1872 እስከ 1862 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር። ማዕረጉ በይፋ «የኡር፣ የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ነበረ።

ሱመር ነገሥታት ዝርዝር ልዩ ልዩ ቅጂዎች ሹ-ኢሊሹ ለ፲ ወይም ለ፳ ዓመታት እንደ ገዛ ሲሉን፣ ፲ የዓመት ስሞች ለእርሱ ተገኝተዋል። የዓመት ስሞቹ ሁሉ ለጣኦታቱ ጌጣጌጥ ወይም ሕንጻዎች ስለ መሥራቱ ናቸው እንጂ ምንም ዘመቻ ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ አይዘግቡም።[1] በ፪ኛው ዓመት ግን የተማረከውን የጣኦት «ናና» ምስል ከአንሻን ወደ ኡር አንዳስመለሰው ይታውቃል። ልጁ ኢዲን-ዳጋን ተከተለው።

ቀዳሚው
እሽቢ-ኤራ
ኢሲንና የሱመር ንጉሥ
1872-1862 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኢዲን-ዳጋን
  1. የሹ-ኢሊሹ ዓመት ስሞች
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.