ሹ-ሲን
ሹ-ሲን ከ1909 እስከ 1901ዓክልበ. ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። የአማር-ሲን ተከታይ ነበር፤ በነገሥታት ዝርዝር ላይ የኡማር-ሲን ልጅ ቢባልም፣ ከሌላ ማስረጃ ግን የታሪክ ሊቃውንት ወንድሙ እንደ ነበር ያምናሉ። ቀድሞ ስሙ እንደ ጊሚል-ሲን ይታነብ ነበር፤ አሁን ግን አጠራሩ «ሹ-ሲን» ትክክል እንደ ሆነ ይታመናል። ንግሥቱ «ኩባቱም» ተባለች።
ለ፱ኝ ዓመቶቹ ሁላቸው በስም ይታወቃሉ፣ እንዲህ፦የሹ-ሲን ዓመት ስሞች
- ሹ-ሲን ንጉሥ የሆነበት አመት። (1909 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን «የአብዙ ዋልያ» የተባለውን መርከብ የሠራበት ዓመት። (1908 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ሲማኑምን ያጠፋበት ዓመት። (1907 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን አሞራውያንን ለመከልከል «የማርቱ ግድግዳ» የሠራበት ዓመት። (1906 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን አሞራውያንን ለመከልከል «የማርቱ ግድግዳ» ከሠራበት ዓመት በኋለ የሆነው ዓመት። (1905 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ታላቅ የጽሑፍ ድንጋይ ለጣኦታቱ ያስቀረጸበት ዓመት። (1904 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥና የአራት ሩቦች ንጉሥ ሹ-ሲን ዛብሻሊ ምድርን ያጠፋበት ዓመት። (1903 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ታላቅ መርከብ ለጣኦታቱ የሠራበት ዓመት። (1902 ዓክልበ.)
- የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ቤተ መቅደስ በኡማ የሠራበት ዓመት። (1901 ዓክልበ.)
በአራተኛው ዘመነ መንግሥት(1906 ዓክልበ.) እንደ ተመለከተ፣ አሞራውያን በአገሩ ውስጥ በጣም በመብዛታቸው ምክንያት፣ እነሱን ለመከልከል ሹ-ሲን ከጤግሮስና ከኤፍራጥስ ወንዞች መኃል ታላቅ ግድግዳ ሠርቶ ነበር። ሹ-ሲን ሴት ልጁን ለአንሻን በኤላም አገረ ገዥ በትዳር ሰጠ። የላጋሽ ኃይለኛ አገረ ገዥ (ሻካናካ) ኢር-ናና ደግሞ የሐማዚ፣ ኡርቢሉምና ሱባርቱ አገረ ገዥ ነበር። በ1903 ዓክልበ. ያጠፋው ዛብሻሊ የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥት ክፍላገር ነበር። ልጁ ኢቢ-ሲን ተከተለው።
ቀዳሚው አማር-ሲን |
የሱመር ነጉሥ 1909-1901 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኢቢ-ሲን |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.