ስምንት
ስምንት በተራ አቆጣጠር ከሰባት የሚከተለው ቁጥር ነው።
ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ፰ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፊደል ኤታ (በትንሹ «Η η») እንደ ተወሰደ ይታመናል።
በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 8 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«ስምንት» ምልክት «VIII» (ወይም viij) ነበር።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.