ሴኬም

ሴኬም (ዕብራይስጥ፦ שְׁכֶם /ሽኬም/) በከነዓን እና በኋላ በእስራኤል የነበረ ከተማ ነው።

  • 2110 ዓክልበ. - አብርሃም በሴኬም ሲያልፍ መስዊያ ለእግዚአብሔር ይሠዋል (ዘፍ. ፲፪)።
  • 2100 ዓክልበ. አካባቢ - በኤብላ የኤብላ ጽላቶች የሴኬም ጣኦት «ራሳፕ» ነው ይላሉ። (የኤብላ ጽላቶች)
  • 1928 ዓክልበ. - የያዕቆብ (እስራኤል) ቤተሠብ ስለ እኅታቸው ስለ ዲና የሴኬም ባላባት ኤዊያዊው ኤሞርን አሸነፈ፤ ሴኬም ሠፈር አጠፋ። (ዘፍ. ፴፬)
  • 1884 ዓክልበ. - የግብጽ ፈርዖን 3 ሰኑስረት በ«መንቱ» (ምድያም)ና በረጨኑ (ከነዓን) ላይ ዘምቶ፣ በ«ሰክመም» (ሴኬም) አሸነፋቸው። (የሰበክ-ሁ ጽላት)
  • 1587 ዓክልበ. - ኢያሱ ወልደ ነዌ በሴኬም ተቀበረ። (ኢያሱ ፳፬)
  • 1360 ዓክልበ. አካባቢ - «ሻክሙ» (ሴኬም) የንጉሥ ላባያ መቀመጫ፣ እርሱ ወታደሮች ከሃቢሩ ወገን ይቀጥራል። (አማርና ደብዳቤዎች)
  • 1252 ዓክልበ. - ጌዴዎን አርፎ ልጁ ከሴኬማዊት ቁባት ጋር፣ አቢሜሌክ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ ሴኬም አመጸበትና ከተማውን አጠፋ። (መሳፍንት ፱)
  • 936 ዓክልበ. - በሰሎሞን መሞት ሴኬም እስከ 915 ዓክልበ. ድረስ የስሜን መንግሥት የእስራኤል መንግሥት መቀመጫ ሆነ። (፩ ነገሥታት)
  • 595 ዓክልበ. - ሴኬም የሳምራውያን ቅዱስ ቦታ ሆነ። (ፍላቪዩስ ዮሴፉስ)
  • 136 ዓክልበ. - ከመቃብያን ወገን ዮሐንስ ሂርቃኖስ የሳምራውያን ቤተ መቅደስ በሴኬም አጠፋ። (ዮሴፉስ)
  • 2 ዓክልበ. - ሴኬም ወደ ሮሜ መንግሥት ሶርያ ጠቅላይ ግዛት ተጨመረ።
  • 25 ዓ.ም. ግድም - ኢየሱስ በ«ሲካር» (ሴኬም) ሲያልፍ መሲህ መሆኑን ለሳምራዊት ይገልጻል። (ዮሕ ፬፡፳፮)
  • 59 ዓ.ም. - ገሊላ በሮማውያን ላይ ሲያመጽ ሴኬም በኬሬያሊስ እጅ ይጠፋል።
  • 64 ዓ.ም. - የሮሜ ቄሣር ቤስጳስያን «ኔያፖሊስ» («አዲስ ከተማ») በሴኬም ሥፍራ አጠገብ አሠራ። ይህ ዛሬ ናብሉስ ይባላል።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.