ሳክሶፎን
ሳክሶፎን አንዳንድ ጊዜም ሳክስ እየተባለ የሚጠራው ዘመናዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በዋናነት የሚሠራው ከነሐስ እና በውስጡ አየርን የሚያስተጋባ ኃይል ያለው ድምፅ እንዲፈጥር ተደርጎ ነው። ይህ መሣሪያ እንደ ክላርኔት ባለ ነጠላ ምላስ መንፊያ አለው። በመሳሪያው ለመጫወት በመንፊያው በኩል አስፈላጊውን ድምፅ የሚመጥን ኃይል ያለው አየር በማስገባት ነው። በመሣሪያው ወገብ ላይ ያሉትን ቁልፎች በእጅ ጣት በመጫን የድምፁን ቅጥነት እና ውፍረት መቀያየር ይቻላል። መሣሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው በቤልጂየማዊው የሙዚቃ ምሁር አዶልፍ ሳክስ ሲሆን የፈጠራ መብቱን (patent) በሕግ ያስመዘገበው ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፰፻፴፰ ዓ/ም ነው።
ገለፃ
ጥቅሞች
ተዛማጅ የሙዚቃ መሣሪያዎች
የውጭ ማያያዣዎች
- Instruments In Depth: The Saxophone Archived ዲሴምበር 13, 2010 at the Wayback Machine በምስል የታገዘ ከBloomingdale የሙዚቃ ትምህርት ቤት (ጁን, 2009)
- Saxophone acoustics ከUniversity of New South Wales.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.