ሲን-ኤሪባም

ሲን-ኤሪባም ከ1753 እስከ 1751 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ ፮ኛ ንጉሥ ነበረ። የሲን-ኢዲናም ተከታይ ነበር። የአባቱ ስም አይታወቅም።

ለዘመኑ ፪ ዓመታት የዓመት ስሞች ታውቀዋል። እነርሱም፦

1753 ዓክልበ. ግ. - «ሲን-ኤሪባም ንጉሥ የሆነበት አመት»
1752 ዓክልበ. ግ. - «ታላቅ የመዳብ ሐውልት ወደ ቤተ መቅደስ ያመጣበት ዓመት»
1751 ዓክልበ. ግ. - «ሲን-ኢቂሻም ንጉሥ የሆነበት ዓመት»

ሲን-ኤሪባም በኒፑር ላይ የላርሳ ሥልጣን አስቀጠለ። የሲን-ኤሪባም ተከታይ ልጁ ሲን-ኢቂሻም ነበረ።

ቀዳሚው
ሲን-ኢዲናም
ላርሳ ንጉሥ
1753-1751 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሲን-ኢቂሻም

የውጭ መያያዣ

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.