ሲን-ሙባሊት

ሲን-ሙባሊት ከ1725 እስከ 1705 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን 5ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን አፒል-ሲንን ተከተለው።

ለሲን-ሙባሊት ዘመን 20 ያህል የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እንግዲህ በ፲፫ኛው ዓመት (1712 ዓክልበ.) ላርሳን እንዳሸነፈ፤ በ፲፮ኛውም ዓመት (1709 ዓክልበ.) ኢሲንን እንደ ያዘ ታውቋል። ይህ የኢሲን ምንግሥት ውድቀት ነበር።

የሲን-ሙባሊት ተከታይ ልጁ ሃሙራቢ ነበረ።

ቀዳሚው
አፒል-ሲን
ባቢሎን ንጉሥ
1725-1705 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሃሙራቢ

የውጭ መያያዣ

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.