ሲንጋፖር
ሲንጋፖር ከተማ-አገር ነው።
ሲንጋፖር ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Majulah Singapura Onward, Singapore |
||||||
ዋና ከተማ | ሲንጋፖር | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ ማላይ ቻይንኛ ታሚልኛ |
|||||
መንግሥት ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
አንድ ፓርቲ አገር ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ ጆሰፍ ዩቫራጅ ፒላይ ሊ ሥየን ሎንግ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
719.1 (176ኛ) 1.43 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የእ.አ.አ. በ2016 ግምት |
5,607,300 (113ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ሲንጋፖር ዶላር (S$) | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +8 | |||||
የስልክ መግቢያ | +65 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .sg .新加坡 .சிங்கப்பூர் |
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 3,438,600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 01°18′ ሰሜን ኬክሮስ እና 10°50′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ታሪክ
የግሪክ መልክዐ ምድር አዋቂ ቶሌሚ (150 ዓ.ም. ግድም) በዚያ ሥፍራ ሳባና የተባለ የንግድ ወደብ በካርታው ላይ አሳየ። በ250 ዓ.ም. ግድም ደግሞ አንድ ቻይናዊ መዝገብ በዚያው ቦታ ፑ ልዎ ቾንግ የተባለ ደሴት ይገልጻል። በ680 ዓ.ም. ገዳማ ደሴቱ በሽሪዊጃያ መንግሥት ግዛት መካከል ሆነ። ከ1300 ዓ.ም. በፊት ተማሲክ የተባለ መንደር ነበረበት። በአንድ ትውፊት ዘንድ ሳንግ ኒላ ኡታማ የሚባል የሽሪዊጃያ መስፍን ያንጊዜ ስሙ ሲንጋፑራ («የአንበሳ ከተማ») የሚባል ከተማ በተማሲክ ደሴት ላይ ሠራ።
በ1400 ዓ.ም. አካባቢ የሽሪዊጃያ መንግሥት ሲደክም ጎረቤቶቹ ማጃፓሂትና ሲያም ይታግሉበት ነበር። ሆኖም ሲንጋፖር ሽሪዊጃያን የተከተለው የመላካ ሡልጣንነት ማዕከል ሆነ። በ16ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ላይ ይህ ሡልጣንነት ከፖርቱጋል ጋር ተጣለና በ1605 ዓ.ም. ፖርቱጊዞች ሲንጋፖርን አቃጠሉት።
የነበረው ከተማ ጠፍቶ ዙሪያው በፖርቱጊዞች ይገዛ ነበር፤ ብዙም ሳያልፍ የሆላንድ ነጋዴዎች ዙሪያውን አስተዳደሩ። የሲንጋፖር ደሴት እራሱ በይፋ በጆሖር ሡልጣን ግዛት ነበር። በ1811 ዓ.ም. የእንግሊዝ አገረ ገዥ ስታምፎርድ ራፈልዝ የሆላንድ ነጋዴዎችን ላዕላይነት ለማቃወም አስቦ ፡ የጆሖር ሡልጣን ጣውንት ወንድሙን ለሡልጣንነቱ ደግፎ ፡ በደሴቱ ላይ አዲስ ከተማ ለመመሥረት ፈቃድ በዚያ አገኙ። የብሪታንያ ቅኝ አገርና ንግድ ጣቢያ ሆኖ በቶሎ አደገ፤ በ1815 ዓ.ም. ጆሖር ደሴቱን ለእንግሊዝ መንግሥት ሸጠው። በብዛት በሲንጋፖር የሰፈሩት ሰዎች ቻይናዊ ነበሩ።
ከ1934 እስከ 1937 ዓ.ም. በ2ኛው አለማዊ ጦርነት የጃፓን ሃያላት ሲንጋፖርን በግፍ ያዙ፤ በዚህም ወቅት የከተማው ስም ሾናንቶ ተብሎ ይሉት ነበር። ከጦርነቱ በኋላ ሲንጋፖር በ1950 ዓ.ም. ራስ-ገዥ ሁኔታ ከእንግሊዝ አገኘ። በ1956 ዓ.ም. ግን በነጻ ፈቃዱ ሲንጋፖር በአዲሱ የመላይዢያ ፌዴሬሽን ውስጥ ክፍል ሆነ። ይህ ሁኔታ እስከ 1957 ዓ.ም. ብቻ ድረስ ቆየ፤ ትብብሩ ለጸጥታ ተስማሚ ስላልሆነም መላይዢያ ሲንጋፖርን ከፌዴሬሽኑ አስወጥቶ የዛኔ እስካሁን ድረስ የሲንጋፖር ሬፐብሊክ ሆነ።
ሕግ
ሲንጋፖር አደንዛሽ የሚከለክል በጣም ጥብቅ ሕግ አለው፣ በአደንዛሽ የሚነግዱ ይሙት በቃ ሊቀበል ይቻላል። የሲንጋፖር ሕግጋት ሁሉ ጥብቅ ናቸው፤ ከባድ ቅጣቶች ይሰጣሉ። ሽንት ቤት ከመጠቀም ቀጥሎ በውሃ ጠርጎ መሄድ እንዳይቀር ክልክል ነው። በገሃድ መትፋት የገንዘብ መቀጫ ያመጣል። ጠበንጃም ሆነ የኪስ ቢላዎ ተከለክለዋል፣ ማስቲካ ስንኳ በሕግ የተከለከለ ሥራ ነው። የሲንጋፖር መንግሥት አንዳንድ ፊልም ብቻ ይፈቅዳል፣ ብዙ ጊዜ በሃይማኖት፣ በዘርኛነት፣ ወይም በእራቁት ምክንያቶች የሚከለክሉ ፊልሞች አሉ።
ባህል
የሲንጋፖር የሚጣፈጥ አበሳሰል ብዙ አይነት የባህር ምግቦችን እንደ ሠርጠን፣ ኦይስተርና ካላማሪ (ስኩዊድ) ያጠቅልላል። በሕንድ ሠፈሮች የአትክልት ቡፌ በሙዝ ቅጠል ላይ ተስፋፍቶ ይቀርባል።
ብዙ በዓላት በሲንጋፖር ይከብራሉ። ጣይፑሳም በተባለው በዓል ቀን ላይ አንዳንድ ሰው የሰውነት መውጋቶች ይሠራል። የቡዲስም፣ እስልምና፣ ክርስትና፣ እና የሕንድ ሀይማኖት በዓላት ሁሉ በሲንጋፖር ይከብራሉ።
ብዙ የክላሲካል ሙዚቃ ወዳጆች በሲንጋፖር ይገኛሉ። ይህን የሚመሰክር በሕዝባዊ አጸዶች ቦታ ውስጥ ለአቀናባባሪው ሾፐን ትዝታ በተሠራው ሐውልት ነው።