ሱሙ-ኤፑኽ
ሱሙ-ኤፑኽ መጀመርያው የምናውቀው የያምኻድ ንጉሥ ነበር። ምናልባት ከ1722 እስከ 1692 ዓክልበ. አካባቢ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) በዋና ከተማው ሐላብ ነገሠ።
ግዛቱ ከሐላብ በላይ አላላኽንና ቱባን ያጠቅልል ነበር።[1][2] ሱሙ-ኤፑኽ በታሪክ መዝገብ መጀመርያው የሚገባ የማሪ ንጉሥ ያኽዱን-ሊም ከጠላቶቹ መካከል ሲጠቅሰው ነው።[3] ያኽዱን-ሊም በአሦር ላይ የማግባባት ስምምነት ከሱሙ-ኤፑኽ ጋር ምንም ቢኖረውም፣ በያምኻድ ስሜንና እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ዘመተ።[4] ስለዚህ ሱሙ-ኤፑኽ በቱቱል ከተማ የሠፈሩት ያሚናውያንን በያኽዱን-ሊም ላይ ደገፋቸው።[5][6] ያኽዱን-ሊምም በዚህ ዘመቻ አሸናፊ ቢሆንም፣ በገዛው ልጅ ሱሙ-ያማን ግድያ ሞተ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የአሦር ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ ማሪን የያዘ ነው።
የአሦር-ያምኻድ ጦርነት
ሱሙ-ኤፑኽ በኻሹም ከተማ እርዳታ በዛልማቁም መንግሥት ላይ ዘመተ።[7] ኻሹም በኋላ ግን ድጋፉን ወደ አሦር አዛወረ፤ እንዲሁም ኡርሹ ከተማና የከርከሚሽ ንጉሥ አፕላሃንዳ ድጋፋቸውን ከያምኻድ ወደ አሦር አዛወሩ። ከዚህ ሻምሺ-አዳድ ማሪን በ1705 ዓክልበ. ይዞ፣ በ1694 ዓክልበ. ልጁን ያስማሕ-አዳድ በማሪ ዙፋን ላይ አስቀመጠው። በተጨማሪ ልጁን ያስማሕ-አዳድን ለቃትና ንጉሥ ኢሺ-አዳድ ሴት ልጅ ለልዕልት በልቱም በማጋባቱ፣ የአሦር-ቃትና ስምምነት አጸና።[8] ያምኻድ በአሦር ጓደኞች ተከቦ ነበር።
የማሪ አልጋ ወራሽ፣ የያኽዱን-ሊም ልጅ ዝምሪ-ሊም ወደ ያምኻድ መንግሥት በስደት ሸሽቶ ሱሙ-ኤፑኽ ሰላምታውን ሰጠው። በማሪ ኗሪዎች አስተያየት፣ ዝምሪ -ሊም በመብት ዕውነተኛ ንጉሣቸው ነበረ።[9] የሻምሺ-አዳድና የጓደኞቹ ሃያላት ሐላብን ለመያዝ ቢሞክሩም አልቻላቸውም። ሱሙ-ኤፑኽ ደግሞ ስምምነት ከሱቴያውያንና ቱሩካውያን ጐሣዎች ጋራ ተዋወሎ እነኚህ አሦርን ከምሥራቅና ደቡብ መቱት።[8] በተጨማሪ ሱሙ-ኤፑኽ የአሦርን አምባ «ዱር-ሻምሺ-አዳድ» አሸንፎ አዲስ ስሙን «ሱር-ሱሙ-ኤፑኽ» ሰየመው።[10]
ሱሙ-ኤፑኽ ምናልባት 1692 ዓክልበ. አካባቢ በዚሁ አሦር ጦርነት ተገደለ።[6] ተከታዩም ልጁ 1 ያሪም-ሊም ነበር፤ እሱም የንግሥቱ የሱሙና-አቢ ልጅ ነበር።
ዋቢ ምንቾች
<div class="reflist references-column-count references-column-count-2" style="
- Trudy Ring,Robert M. Salkin,Sharon La Boda (1995). International Dictionary of Historic Places: Southern Europe. p. 10. http://books.google.nl/books?id=74JI2UlcU8AC&pg=PA10&dq#v=onepage&q&f=false.
- Sarah Melville,Alice Slotsky (2010). Opening the Tablet Box: Near Eastern Studies in Honor of Benjamin R. Foster. p. 376. http://books.google.nl/books?id=2aq43z3at0wC&pg=PA376#v=onepage&q&f=false.
- Douglas Frayne (1990). Old Babylonian Period (2003–1595 BC). p. 780. http://books.google.nl/books?id=u2nUT_RtyQ8C&pg=PA780#v=onepage&q&f=false.
- Mario Liverani (2013). The Ancient Near East: History, Society and Economy. p. 354. http://books.google.nl/books?id=_EtJAgAAQBAJ&pg=PT354#v=onepage&q&f=false.
- Arne Wossink (2009). Challenging Climate Change: Competition and Cooperation Among Pastoralists and Agriculturalists in Northern Mesopotamia. p. 128. ISBN 9789088900310. http://books.google.nl/books?id=Oy4xUpsa7DkC&pg=PA128#v=onepage&q&f=false.
- Trevor Bryce (2013-03-07). The Routledge Handbook of the Peoples and Places of Ancient Western Asia. p. 773. ISBN 9781134159086. http://books.google.nl/books?id=E1aF0hq1GR8C&pg=PA773#v=onepage&q&f=false.
- Sidney Smith. Anatolian Studies: Journal of the British Institute of Archaeology at Ankara. Special number in honour and in memory of John Garstang, 5th May, 1876 - 12th September, 1956, Volume 6. p. 38. http://books.google.nl/books?id=sNOKQgAACAAJ&dq.
- William J. Hamblin (2006-08-20). Warfare in the Ancient Near East to 1600 BC. p. 171. ISBN 9780203965566. http://books.google.nl/books?id=h5IQQir5eFEC&pg.
- William J. Hamblin (2013-01-11). Warfare in the Ancient Near East to 1600 BC. p. 259. ISBN 9781134520626. http://books.google.nl/books?id=h5IQQir5eFEC&pg.
- Horst Klengel. Syria, 3000 to 300 B.C.: a handbook of political history. p. 52. http://books.google.nl/books?ei=sqwxU5fpCIrb0QXlqYC4Dg&hl=nl&id=5GptAAAAMAAJ&dq.
ቀዳሚው ? |
የያምኻድ ንጉሥ 1722 – 1692 ዓክልበ. ግ. |
ተከታይ 1 ያሪም-ሊም |