ሰዋጅካሬ
ሰዋጅካሬ ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1796 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰኸተፒብሬ ተከታይ ነበረ።
ሰዋጅካሬ | |
---|---|
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1796 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰኸተፒብሬ |
ተከታይ | ነጀሚብሬ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
ስሙ ከቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ብቻ ይታወቃልና ሕልውናውን የሚያስረዳ ቅርስ ገና አልታወቀም። በዝርዝሩም «ሰዋጅካሬ ለ<...>ና ለ፲፩ (ወይም ፲፬?) ቀን ነገሠ» ሲል በአቶ ራይሆልት ግመት ከጥቂት ወር በላይ አይሆንም። በርሳቸው ግመት ተከታዩ ነጀሚብሬ ነበር። በዚሁም ወቅት ባጭር ጊዜ ውስጥ አያሌ ፈርዖኖች እንደ ጠፉ ይመስላል።
ቀዳሚው ሰኸተፒብሬ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1796 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ነጀሚብሬ |
ዋቢ ምንጭ
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.