ሰዋጅተው

ሳንኸንሬ ሰዋጅተውላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1659 እስከ 1656 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ሰዋጅተው
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1659-1656 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ መርሆተፕሬ ኢኒ
ተከታይ መርሰኸምሬ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ስሙ የታወቀው በቶሪኖ ቀኖና ሰነድ፣ ከመርሆተፕሬ ኢኒ ቀጥሎ ስለ ተዘረዘረ ብቻ ነው። ሦስት አመትና ሁለት ወር እንደ ነገሠ ይላል። በተረፈ ስለዚሁ ፈርዖን አንዳችም አልተገኘም።

በዚሁ ዘመን የሥርወ መንግሥቱ ሥልጣን ከጤቤስ ከተማ በጣም እንዳልራቀ፣ ሂክሶስም ወገኖች በስሜን እንደ ገዙ ይታስባል።

ቀዳሚው
መርሆተፕሬ ኢኒ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1659-1656 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መርሰኸምሬ

ዋቢ ምንጭ

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.