ሰኸተፕካሬ አንተፍ
ሰኸተፕካሬ አንተፍ ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1754 እስከ 1744 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የስመንኽካሬ ኢሚረመሻው ተከታይ ነበረ።
ሰኸተፕካሬ አንተፍ | |
---|---|
የ«ኸተፕካሬ» ማኅተም | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1754-1744 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው |
ተከታይ | ሴት መሪብሬ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ እንዲሁም በካርናክ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ተዘገበ። ሕልውናውም ከአንዳንድ ቅርስ ተረጋግጧል። ብዙ ሌላ መረጃ አይታወቅም።
ቀዳሚው ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1754-1744 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሴት መሪብሬ |
ዋቢ ምንጭ
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.