ሰኸምካሬ 5 አመነምሃት
5 አመነምሃት ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1811 እስከ 1808 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የነሪካሬ ተከታይ ነበረ።
5 አመነምሃት | |
---|---|
በሙኒክ ሙዚየም ያለ የፈርዖን ራስ «አመነምሃት ፭» ሲባል፣ ይህ መታወቂያ ግን አልተረጋገጠም። | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1811-1808 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | ነሪካሬ |
ተከታይ | አመኒ ቀማው |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስረዳው፣ የቶሪኖ ቀኖና የተባለው ነገሥታት ዝርዝር «ሰኸምካሬ ...[ሶንበ]ፍ...፣ ...፣ አመነምንሃት ...ሬ» ይላል። አለዚያ ለዚህ አመነምሃት የተረጋገጠ ቅርስ የለም።
አንድ ሐውልት ተገኝቶ «ንጉሥ ሰኸምካሬ የንጉሥ አመነምሃት ልጅ» ተጽፎበት ስለ ተገኘ፣ የዚህ ፭ አመነምሃት ሌላ ስም «ሰኸምካሬ» እንደ ነበር ተገመተ። ሆኖም ይህ ምስል የቀዳሚው የሰኸምካሬ ሶንበፍ ሐውልት ይመስላል። በብዙ መምህሮች አስተሳሰብ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች (ሶንበፍ እና ፭ አመነምሃት) አንድ ፈርዖን ነበሩ። «የጨለማ ዘመን» በመሆኑ ለዚሁ ወቅት የመዝገቦች ጉድለት አለ።
ቀዳሚው ነሪካሬ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1811-1808 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ አመኒ ቀማው |
ዋቢ ምንጭ
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.