ሰንበት

ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?

ሰንበት ማለት አቆመ፣ አረፈ ማለት ነው፡፡ይህ ቀን የጌታ ዕረፍት የተባረከም ቀን ነው፡፡ከማንኛውም ሥጋዊ ሥራ ተቆጥበን የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስብበት ቀን ነው፡፡ ሰው እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ የሰንበት ቀንም የተፈጠረው ለዚህ ነው፡፡ (ዘዳ

5፥14)፣(ማር 2፥38)

ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለእረፍት የተቀደሰው

የተባረከው ዕለት ሰንበት ብቻ ነው፡፡ ስለሌሎች ቀናት

የተነገረው ‹‹ ያ መልካም እንደሆነ አየ››የተባለው ብቻ ነው፡፡

ሰንበትን ግን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ (ዘፍ 1፥12፣ 18፥20፣

25፥31)

በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያን ሁለት ሰንበት አለ ቀዳሚት ሰንበት

(ቅዳሜ) እና ሰንበተ ክርስቲያን(እሑድ)

1. ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) ጌታ ያረፈባት ለእስራኤል ዘሥጋ

የታዘዘው ሰንበት ነው፡፡

ይህ ቀን እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አምላክ ከግብፅ

ባርነት ወደ እረፍት እንዳወጣቸው ያመለክታል፡፡(ዘዳ

5፥2-16) በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ

ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ 3፥

17) ፣ (ሕዝ 20፥12) ፣ (ዘኁ 15፥32-36)

ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን

እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር፡፡ስለዚህም በጌታችን

በኢየሱስ ክርስቶስ ተወቅሰዋል፡፡ (ማቴ 12፥14) ፣ (ሉቃ 4፥

16)

በዘመነ ሐዲስ የክርስቲያኖች የቀዳሚት ሰንበት አከባበር እንደ

አይሁድ ለሰው የሚከብድ እንዳይሆን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ

19 ላይ ተገልጿል፡፡

2. ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)

እሑድ ማለት አሐደ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን

ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ

ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡

ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10) ፡፡

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ “ዕለተ እግዚአብሔር” የሚላት

ዕለተ እሑድ ናት፡፡

ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-

- እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ

ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና።

- ዕለተ ሥጋዌ ናት፦ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት

የፍሰሐ ቀን፡፡

- ዕለተ ትንሣኤ ናት፦ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት

- የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፦ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት

የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያኙባት ዕለት።

-ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን

መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ

ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት።

ናት (1ኛ ቆሮ 16፥1)

-የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን

ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፥7)

በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ

የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ

አስነግሮ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን

መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት

(የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት

የሚያቀርቡበት ቀን ነበር፡፡ (ራዕ 1፥10)

በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ

ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ

ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት

የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ

4፥1-10)

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.