ሰንሰለት

ሰንሰለት ማለት በተርታ የተያያዙ የብረት ቀለበቶች ማለት ነው። አንድ ሰንሰለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቀለበት ሊኖረው ይችላል።

የቀለበት ሰንሰለት
ተሽከርካሪ ሰንሰለት

ሰንሰለቶች በሁለት አይነት መንገድ ትልማቸው ይከናወናል።

፩- በሁለት ቅጥ መተጣጠፍ የሚችሉ። እኒህ እንግዲህ አብላጫውን ጊዜ የቀለበት ሰንሰለት ሲሆኑ እቃ ለማንሳት እና ነገሮችን ለማሰር ይረዳሉ። ስለሆነም በሁለት ቅጥ አቅጣጫወች መልመጥመጥ እንዲችሉ ተደርገው ይሰራሉ።

፪- በአንድ ቅጥ ብቻ መታጠፍ የሚችሉ። እኒህ ብዙ ጊዜ ሃይልን ከአንድ ማሽን ወደ ሌላ ማሽን ለማስተላለፍ ሆን ብለው የሚሰሩ ናቸው። ስለሆነም ትልማቸው የሌላ ማሽን ጥርስን ለመንከስ እንዲችሉ ተደርገው ነው። ለምሳሌ የብስክሌት ፔዳል ሰንሰለት አንዱ ነው። እኒህ አይነቶቹ ሰንሰለቶች በአንድ ቅጥ ብቻ ይልመጠመጣሉ።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.