ሰኔ ፭
ሰኔ ፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፸፭ኛው ቀን ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፸ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፺፩ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፺ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በቻይና የሲቹዋን ግዛት ውስጥ ከአሥር ቀናት በፊት የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ምክንያት በድንጋይና አፈር ናዳ ተገድቦ የነበረው ‘ዳዱ’ የተባለው ወንዝ ይሄንኑ ግድብ ጥሶ ሲሄድ መቶ ሺ ያህል ሰዎች በጎርፉ ተጥለቅልቀው ሞተዋል።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፑብሊክ የቀድሞው አምባ-ገነን ‘ቄሳር’፣ ዣን ቤደል ቦካሳ በአሥራ ሦስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ጊዜያት ለፈጸሟቸው ወንጀሎች የሞት ቅጣት ተፈረደባቸው።
ልደት
ዕለተ ሞት
- ፲፰፻፺፬ ዓ/ም - አለቃ ገብረሐና ገብረ ማርያም ባደረባቸው ህመም በዚህ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.