ሰኔ ፩
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፸፩ኛው ቀን እና የፀደይ/በልግ ፷፮ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፺፭ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፺፬ ቀናት ይቀራሉ።
ሰኔ ፩ ቀን
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በአይስላንድ የሚገኘው ላኪ የተባለው ተራራ በእሳተ ገሞራ ፈንድቶ ከ ፱ ሺ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በአገሪቱ ላይ የሰባት ዓመት ረሀብ አስከተለ።
- ፲፰፻፭ ዓ/ም - የሸዋው መርዕድ አዝማች ወሰን ሰገድ አርፈው በቁንዲ ጊዮርጊስ ተቀበሩ። ልጃቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አልጋውን ወረሱ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - በኢጣልያ አስተናጋጅነት የተካሄደው ሁለተኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውድድር የመጨረሻው ጨዋታ በኢጣልያ እና ቼኮዝሎቫኪያ ቡድኖች ግጥሚያ ሲሆን ኢጣልያ ፪ ለ ፩ አሸንፋ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፴፪ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት ከደብረ ወርቅ ብዙ ጓዝና መሣሪያ ጭኖ ወደ ቢቸና ሲጓዝ የነበላይ ዘለቀ አርበኞች ገጥመውት ከፍተኛ ውጊያ ተደርጎ አርበኞቹ ድል አድርገውት ብዙ መሣሪያ ማረኩ።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - ለአሜሪካ ጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ የነበሩትን ማርቲን ሉተር ኪንግን የገደለው ጄምስ ኧርል ሬይ በሂዝሮው የሎንዶን አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ ተያዘ።
ልደት
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/June_8
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.