ሰኔ

ሠኔ የወር ስም ኾኖ በግንቦት እና በሐምሌ ወራት መኻል የሚገኝ ከዐሥራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ አሥረኛው የወር ስም ነው። «ሠኔ» ከግዕዙ «ሠነየ» ከሚለው ቃል የተባዛ ሲኾን አስጊያጭ፥አሳማሪ ማለት ነው።[1] የሠኔ ወር የክረምት የመጀመሪያው ወር ሲኾን ከግንቦት ደረቃማነት በኋላ በዝናም ርጥበት መሬቷ በአረንጓዴ የምታምርበት ወቅት ነው።

የሰኔ ቀናት
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30

በሠኔ ወር ነጻነታቸውን የተቀዳጁ የአፍሪቃ አገሮች

በሠኔ ወር በጠቅላላው ዐሥራ ኹለት የቅኝ ግዛት አገሮች ነጻነታቸውን አግኝተዋል። ከነዚህም ዐምስቱ በፈረንሳይ፤ ሦስቱ በብሪታንያ፤ ሦስቱ በቤልጂግ እና አንድ በኢጣልያ አስተዳደር ሥር ነበሩ።

ዘመን

  1. ዘመነ ማቴዎስ
  2. ዘመነ ማርቆስ
  3. ዘመነ ሉቃስ
  4. ዘመነ ዮሀንስ


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ

ዋቢ ምንጮች

  1. [http:// http://gzamargna.net/html/gs.html]
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.