ሬት

ሬት (Aloevera) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ወገን ነው።

ሬት

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ደማቅ ቢጫና ቀይ አበቦች አሉት።

ብዙ ዝርያዎች አሉ፤ ከሁሉ የታወቀው Aloe vera ወይም «እውነተኛ ሬት» ነው።ሬት የተለያየ ዝርያ ያለዉ ተክል ሆኖ በብዛ ለዉበት ግብዓቶች መስሪያ አልግሎት ላይ የሚዉል ነዉ፡፡ ይህ የተክል ዝርያ ኢትዮጵያ ዉስጥም በብዛት እንደሚገኝ ይገመታል፡፡ሬት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን አስካሁን ባለዉ ጥናት በጤናዉ ዘርፍና በዉበት መጠበቂያ ኢነዱስተሪዉ ዘርፍ በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ዉስጥ እዚህ ግባ የሚባል አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እንደ ማህረሰብ ለሬት ያለን አረዳድ እና የሚደረገዉ ጥናትም እጅግ አናሳ መሆኑ ነዉ፡፡

  • አልጌ A. macrocarpus ብዙ ጊዜ «ቃጫ» ሲባል፣ ቃጫ በደንብ የሌላው ተክል ስም ነው።
  • የሴት ሬት A. pulcherima
  • ወንድ ሬት A. trichosantha

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ብዙ ዝርያዎች በኢትዮጵያ አሉ። ለአፍሪካ፣ ማዳጋስካር፣ አረቢያ ኗሪ ናቸው፤ አሁንም ተክሎቹ በተለይም እውነተኛ ሬት የትም አገር ይገኛሉ።

የተክሉ ጥቅም

ወፍራም ቅጠሉ ሆድን የምታነጻ መድሃኒት ነው፣ ትኩሳትንም ያቀዝቅዛል፣ የጣፊያና የጉበት ችግሮች፣ የጉልበት ችግሮችም፣ ለማከም ይጠቀማል።

ፈሳሹ ደግሞ ለዓይን ሕክምና ተጠቅሟል። ስለ መራራነቱ እናቶችም ለሕሳናት ጡት ማስወጫ ተጠቅመውታል።

የተከተፈ እሬት በጨው ለፍየልና ለበግ ማለፊያ መኖ ይሠራል።[1]

ውጡም እንደሚያስቀምጥ መድሃኒት ይቆጠራል። በተለይ በአለም ዙሪያ ዕውነተኛ ሬት ለቆዳ ችግሮች እንደ መቃጠሎች እንዲረዳ ይታመናል።

ደባርቅ በተደረገ ባህላዊ ህክምና ጥናት ዘንድ፣ አንድ የኢትዮጵያ ዝርያ A. percrassa የእሬት ሥር ተደቅቆ በማር ተቀላቅሎ ተፍሎም ለ፫ ቀን ለመሳል ይወሰዳል። እንዲሁም የዚህ ዝርያ የቅጠሉ ውጥ ለአህያ ኪንታሮት መታገስ ይለጠፋል።[2]

  1. አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. እስክዳር አበበ - የደባርቅ ባህላዊ ሕክምና 2003 ዓም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.