ሪቻርድ ኒክሰን

ሪቻርድ ሚልሆስ ኒክሰን (ከጃንዌሪ 9፣ 1913 እ.ኤ.አ. እስከ ኤፕሪል 22፣ 1994 እ.ኤ.አ. የኖሩ) ከ1969 እስከ 1974 እ.ኤ.አ. (1962-1966 ዓ.ም.) ባለው ጊዜ ውስጥ 37ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።

ከአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ማዕረጋቸን የተዉት እሳቸው ብቻ ሆነው፤ ምክትላቸው ጄራልድ ፎርድ የዘመናቸውን ትርፍ ጨረሱ።

መንግሥታቸው በሁከቶች የተመላ ነበር። ከመጀመሩ ቀዳሚው ሊንደን ጆንሰን ጦርነት በቬት ናም አወረሷቸው። ይህም ጦርነት በአሜሪካ ውስጥ ብዙ ተቃራኒዎች ነበሩት። ኒክሰን ግን ጦርነቱን ስላልጨረሱት፣ ነገር ግን ወደ ላኦስካምፖድያ ስላስፋፉት፣ ለሰላም የሚጮህ ወገን በሃይል ሠለፉ። በሠልፎቹ ጫፍ በኤፕሪልና በመይ 1971 እ.ኤ.አ.፣ በዋሺንግቶን ዲሲ የጸረ ጦርነት ሰልፈኞች እጅግ በዙና ከተማው ተሞላባቸው። ሠራዊቱ ተጠራና ፖሊሶቹ ከ12 ሺ በላይ ያዙ። ኒክሰን ከዚህ በኋላ ጦርነቱን አስጨረሱ፣ ለሁለተኛ ዘመን በ1972 እ.ኤ.አ. ተመረጡ። በዚህ ዘመን በዋተርጌት ቀውስ በወንጄል ተከሰሱና ማዕረጋችውን ተዉ።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.