ሩዝ

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የምግብ አይነት ሲሆን፣ የሚሰራውም ከሩዝና ሱጎ ነው።

አዘገጃጀት

ሩዝ በስጋ ሶስ (ለ3 ሰው) አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች  3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ሩዝ  3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ጐረድ፣ ጐረድ ተደርጐ የተከተፈ ለስላሳ የበሬ ስጋ  ግማሽ መካከለኛ ጭልፋ የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት  1 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት  2 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ  1 የሻይ ማንኪያ በርበሬ  4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ  ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው  1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ

አዘገጃጀት 1. በደረቅ ብረት ድስት ቅቤውን ማሞቅ፣ በተጓዳኝ ሩዙ እንዲበስል ለብቻው በሌላ ብረት ድስት መጣድ፤ 2. ቅቤው ላይ ስጋውን ጨምሮ መጥበስ፤ 3. ቀይ ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ ውኃው በደንብ እስኪመጥ ማቁላላት፤ 4. የቲማቲም ድልህና በርበሬ መጨመር፤ 5. ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ መረቅ እንዲኖረው አድርጐ እንዲበስል መተው፤ 6. ሩዙ በስሎ ውኃውን ሲመጥ ወደተዘጋጀው ሶስ ጨምሮ እንዳይቦካ በዝግታ ማማሰል፤ 7. ለገበታ ሲፈለግ በትኩሱ ጐድጐድ ባለ እቃ ማቅረብ፡፡

ሊተረጎም የሚገባ

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.