ሥነ-ፍጥረት

ያስገቡ

ፍጥረታት የተገኙበት መንገድና ሁኔታ

ፍጥረታት የተገኙበት ሁኔታ በሁለት ሁኔታ ነው፡፡ እነርሱም እምኸኀበ አልቦ አልቦ ኀበቦ (ካለመኖር ወደመኖር) በማምጣት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ግብር እም ግብር ከተፈጠሩት ላይ በመፍጠር ነው፡፡

  • እምኀበ አልቦ ኀበቦ(ካለመኖር ወደ መኖር) በማምጣት የፈጠራቸው ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ማለትም ነፋስእሳትውሃመሬትጨለማመላእክት ናቸው፡፡
  • ግብር እም ግብር (ከተፈጠሩት ላይ በመፍጠር) የተፈጠሩት ደግሞ ሌሎቹ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መገኛቸውም አራቱ ባሕርያተ ስጋ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እነሱን በማዋሐድ ፈጥሯቸዋል፡፡

ፍጥረታት የተገኙበት መንገድ ደግሞ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-

  1. በዝምታ /በአርምሞ/፡- አራቱ ባሕሪያተ ስጋ፣ ጨለማ፣ መላእክት፣ ሰማያት
  2. በመናገር /በነቢብ/፡- ብርሃን፣ የዕለተ ሰኞ፣ የዕለተ ማክሰኞ፣ የዕለተ ረቡእ እና ሐሙስ ሥነ-ፍጥረታት ናቸው፡፡
  3. በመስራት /በገቢር/ ፡-ሰውን ብቻ፡፡

የስድስት ቀናት ፍጥረታት

የእለተ እሑድ ፍጥረታት፡- እሑድ ማለት አሐደ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን የመጀመሪያ አንደኛ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ቀን ስምንት ፍጥረታትን እምኀበ አልቦ ኀበቦ አምጥቶ እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃ፣ አፈር/መሬት፣ ጨለማ፣ ሰማያት፣ መላእከት እና ብርሃን ናቸው፡፡ /ዘፍ.1፣1 እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃና መሬት አራቱ ባሕርያተ ስጋ ይባላሉ፡፡ ሰማያት ሰባት ናቸው፡፡ /መዝ.18፣1 ማቴ.3፣17 2ኛ ቆሮ.123 ዮሐ.14፣2 ዕዝራ ሱቱኤል 4፣4/

  1. ጽርሐ አርያም፡- ከሰማያት ሁሉ በላይ ናት፡፡ ለመንበረ መንግስት እንደ ጠፈር የምታገለግል ናት፡፡
  2. መንበረ መንግስት /መንበረ ስብሐት/፡- እግዚአብሔር በወደደው ምሳሌ ለፍጡራን የሚታይበት ነው፡፡ ለኢሳይያስሕዝቅኤልወንጌላዊው ዮሐንስ በአምሳለ ንጉስ ታየቷቸዋል፡፡ ኢሳ.6፣1 ሕዝ.12፣6 ራዕ.4፣2 መዝ.10፣4 ሰማይ ውዱድን እንደ መሰረት አድርጎ ሰርቷታል፡፡
  3. ሰማይ ውዱድ፡- ከኪሩቤል ላይ ተዘርግቶ ለመንበረ መንግስት እንደ አዳራሽ ወለል ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡
  4. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፡- በፊት ሳጥናኤል የተፈጠረበት ኋላ የወጣባት ናት፡፡ ራዕ.12፣9 ይሁ.1፣6 በእለት ምጽአት በጎ የሰሩ ሰዎች የሚወርሷት የክርስቲያኖች ርስት ናት፡፡ ገላ.4፣4-26 ዕብ.12፣22 ዮሐ.14፣2 አስራ ሁለት ደጅ አላት፡፡ የደጆቿም ብርሃን ለዓይን እጅግ የሚስቡ ናቸው፡፡ የብርሃን መጋረጃም አላት፡፡ የ12ቱ ሐዋርያቱም ስም በመሰረቶቿ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እግዚአብሔር የብርሃን ታቦትን ፈጥሮ አኑሮባታል፡፡የአምላክ ማደሪያ የሆነች ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ /ራዕ.11፣19/
  5. ኢዮር
  6. ራማ
  7. ኤረር፤ እነዚህ ሦስቱ ዓለመ መላእክት /የመላእክት መኖሪያ/ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በ3 ክፍል የምትሰራው በዚህ ምሳሌ ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት

መላእክት የተፈጠሩ በመጀመሪያ ቀን በእለተ እሑድ ነው፡፡ /ኩፋ.2፣6-8 በነገድ መቶ በከተማ አስር ነበሩ፡፡ መላእክት እምኀበ አልቦ ወይም ከአምላካዊ ብርሃን ተፈጥረዋል፡፡ አክሲማሮስ የተባለ መጽሐፍ መላእክት ከነፋስ ከእሳት ተፈጥረው ቢሆኑ እንደኛ ሞተው በፈረሱ በበሰበሱ ነበር ብሏል፡፡ በቅዱሳት መጽሐፍት በግብራቸው በእሳትና በነፋስ ተመስለዋል፡፡ መዝ.103፣4 ዕብ.1፣7 በእሳትና በነፋስ መመሰላቸው ነፋስ ፈጣን ነው መላእክትም ለተልእኮ ይፈጥናሉና፡፡ ነፋስ ረቂቅ ነው መላእክትም ረቂቃን ናቸው፡፡ እሳት ብሩህ ነው መላእክትም ብሩኀነ አእምሮ ናቸው፡፡ የመላእክት ባሕርይ ፦

  • መላእክት በፍጥረታቸው ረቂቃን ስለሆኑ ስጋና አጥንት የላቸውም፡፡ አይበሉም አይጠጡም /ሉቃ.24፣39/
  • መላእክት ጾታ የላቸውም፡፡ አያገቡም፡፡ /ማቴ.22፣30
  • አንድ ጊዜ የተፈጠሩ የማይባዙ የማይዋለዱ ናቸው፡፡ ህማም ሞትና ድካም የለባቸውም ሕያዋን ናቸው፡፡
  • ቁጥራቸው በአኃዝ አይወሰንም /ራዕ.5፣11/

የመላእክት ግብራቸው /ስራቸው/

  • ስራቸው እግዚአብሔርን ያለ እረፍት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሌትና ቀን ማመስገን ነው፡፡ /ኢሳ.6፣3 ራዕ.4፣8/
  • መላእክት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ለምህረትና ለብስራታ ለቁጣም ይላካሉ፡፡ /ሉቃ.1፣1-26 ዘፍ.19፣1-38፤ 2 ነገሥ.19፣35…/
  • ድኀነት የሚገባቸውን ሰዎች ይጠብቃሉ /መዝ.33፣7 90፣15/ ማቴ.18፣10 የሐ.ሥራ 12፣7/
  • ክፉዎችን ይቃወማሉ፡፡ የሐሰትና የዓመጸኛ የክህደት ምንጭና አባት የሆነውን ዲያብሎስን /ሄኖክ.12፣3 መቅ.ወንጌል ራእይ. 13፣5 ዮሐ. 8፣44/ በመጀመሪያ የተቃወሙት መላእክት ናቸው፡፡ /ራዕ.12፣7/
  • የቅዱሳንን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳረጋሉ፡፡ /ራዕ.8፣2-4 ጦቢ.12፣15/
  • መላእክት ሰውን ያማልደሉ፡፡ ሰው ከፈጣሪው ጋር እንዲታረቅ ይጸልያሉ፡፡ የእግዚአብሔር ባለሟሎች ናቸውና ስለ ሰው ይለምናሉ፡፡ [1]
  • መላእክት ሰውን ይረዳሉ፡፡ /ዘፍ 16፣7 21፣17፤ 1 ነገሥ.19፣5-7/ ሰውን ይጠብቃሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ሁለት ጠባቂዎች አሉት፡፡ አንዱ መላእክ ቀን አንዱ ደግሞ ሌሊት ይጠብቁታል፡፡ /ማቴ.18፣10/
  • የእግዚአብሔር አገልጋዮችን በችግራቸው ጊዜ ይረዳሉ ያበረታሉ፡፡ /የሐዋ.5፣12-24 12፣1-17 27፣22-25/
  • መላእክት ንስሃ በሚገቡ ሰዎች ደስ ይሰኛሉ፡፡ /ሉቃ.15፣10/
  • መላእክት ይህን የመስላሉ ቁመታቸው ይህን ያህላል ማለት አይቻልም ፡ ረቂቃን ናቸውና ሊያድኑ ያሉትን ለመታደግ በወጣትና በሽማግሌ በተለያዩ አምሳላት ይታያሉ፡፡

የሰኞ /ሁለተኛው ቀን/ ስነ ፍጥረት

ሰኞ ማለት ሰኑይ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን በሁለተኛው ቀን እግዚአብሔር ከምድር እስከ ብሩህ ሰማይ ሞልቶ የነበረውን ውኃ ወደ ላይና ወደ ታች ከፈለ፡፡ በመካከሉም ጠፈርን አደረገ፡፡ ጠፈርንም ሰማይ ብሎ ጠራው፡፡ ከጠፈር በላይ የተቀረውም ውኃ ሐኖስ ይባላል፡፡ ዘፍ.1፣6-8 ኩፋ.2፣9 የጠፈር ጥቅም፦

  • ፀሐይ፣ ለከዋክብትና ለጨረቃ መመላለሻ ማኀደር ይሆን ዘንድ
  • ከፀሐይ ከጨረቃና ከክዋክብት የሚወጠው ብርሃን ጉብብ ባለ ቅርጽ ወደላይ ሳይነዛ ወስኖ ገትቶ እንዲይዝ
  • ወአየ ፀሐይን (ሙቀት ማፋጀት) እንዲያቀዘቅዝ
  • ሰው ጠፈርን ወይም ሰማይን እያየ ሰማያዊ ርስቱን ተሥፋ እንዲያደርግ
  • ለአይናችን ማረፊያ

ማክሰኞ /የሦስተኛው ቀን/

ማክሰኞ የሚለው ቃል ሠሉስ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦሥትኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ፍጥረታት ከተፈጠሩ ሦስተኛ ቀን ነውና ሌላው ደግሞ ማክሰኞ የሚለው ቃል ማግሰኞ (የሰኞ ማግስት) ማለት ነው፡፡ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ ብሎ ውኃን ከመሬት ለይቶ ባህር ካለው በኋላ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ ዘፍ. 1፣9-13 ኩፋ.2፣10-12፡፡ እነርሱም ፡- እጽዋትአዝእርትአትክልት ናቸው፡፡

  • ምሳር የሚቆረጡ እጽዋት /ዛፎች/፡፡
  • ማጭድ ሚታጨዱ አዝርዕት፡፡
  • በእጁ የሚለቀሙ አትክልት ናቸው፡፡
  • ገነት ተክል

ዕፅዋት አዝርእትና አትክልት ከአራቱ ባሕርያት ከመሬት ከውኃ ከነፋስ እና ከእሳት ተፈጥረዋል ይኸውም በግብራቸው ይታወቃሉ፡፡ የዚህ እለት ፍጥረታት ለምስጢረ ስጋዌ ምሳሌ እንጠቀምበታለን፡፡

የረቡዕ /የአራተኛው ቀን/

ሥነ-ፍጥረት እለት ረቡእ ራብዕ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን አራተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ሥነ ፍጥረታት ከተፈጠሩ አራተኛ ቀን ማለት፡፡ በእለተ ረቡዕ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነዚህም፡- ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት ናቸው። /ዘፍ.1፣14-16/ ከዋክብትና ጨረቃን በሌሊት ፀሐይን በቀን አሰለጠናቸው /መዝ.135፣8-9/። ፀሐይ ከእሳትና ከነፋስ በመፈጠሯ ትሞቃለች ትሄዳለች፡፡

ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩት ከነፋስና ከውኃ ነው፡፡ ከነፋስ በመፈጠራቸው ይሄዳሉ፣ ከውኃ እንደመፈጠራቸው ደግሞ ይቀዘቅዛሉ፡፡ እነዚህንም ለዕለታት ለሳምንታት ለወራት ለአመታትና ለክፍለ ዘመናት መታወቂያ መለያ እንዲሆኑ ፈጥሮአቸዋል /ኩፋ.2፣13-14/፡፡ የዚህ እለት ፍጥረታት ለምስጢረ ትንሳኤ ሙታን ምሳሌ እንጠቀምባቸዋለን፡፡

የሐሙስ /የአምሰተኛ ቀን/ ፍጥረት

ሐሙስ የሚለው ቃል ሃምሳይ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አምሰተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ አምስተኛ መባሉም ፍጥረታት ከተፈጠሩ አምስተኛ ቀን ሆኗልና፡፡ በእለተ ሐሙስ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ በልብ በሚሳቡ፣ በእግር የሚሽከረከሩ በክንፍ የሚበሩ በባህር ተወስነው የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕይወት ሕያዋን የሆነ ፍጥረታትን ፈጠረ። /ዘፍ.1፣20-23 ኩፋሌ.2፣15-16 እነዚህም ዘመደ እንስሳ፣ ዘመደ አራዊት፣ ዘመደ አእዋፋት ይባላሉ፡፡

  • ዘመደ እንስሳ፡-አሳዎች
  • ዘመደ አራዊት፡- አዞ
  • ዘመደ አእዋፋት፡- ዳክዬዎች

የእለተ ዓርብ ቀን ሥነ-ፍጥረት

አርብ ማለት አርበ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አካተተ ፈጸመ ማለት ነው፡፡ በእለተ አርብ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታትን ፈጥሮ ጨርሷልና በዚህ ቀን እግዚአብሔር አራት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነርሱም በእግር የሚሽከረከሩ በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ በየብስ የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕይወት ሕያዋን የሆኑ ፍጥረታትን ፈጠሩ፡፡ በመጨረሻም አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ሰውን በመልካችን እንፍጠር ብለው ዓርብ እለት በነግህ አራቱን ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አዋህደው የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርጎ በማዕከለ ምድር /መዝ.73፣12/ በቀራኒዮ አዳምን ፈጠሩት፡፡

  • እንስሳት፡- ሳር ነጭተው ውኃ ተጎንጭተው የሚኖሩ
  • አራዊት፡- ሥጋ በጭቀው ደም ተጎናጭተው ውኃ ጠትተው የሚኖሩ
  • አዕዋፋት፡- የዛፍእህልን ፍሬ ለቅመው ሥጋ በልተው ውኃ ጠጥተው የሚኖሩ ናቸው፡፡

አዳም ማለት ይህ ቀረው የማይባል ያማረ መልከ መልካም ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ከመሬት መፈጠሩን ያመለክታል፡፡ ሰው አራት ባሕርያተ ስጋ አምስተኛ ግብራተ ነፍስ አሉት፡፡

  • የነፍስ ግብራት፡- ልባዊነት፣ ነባቢነት፣ ሕያውነት
  • ባሕርያተ ሥጋ፡- ውኃ፣ መሬት፣ ንፋስና እሳት

አዳም በተፈጠረ በሳምንቱ ጠዋት ሦስት ሰዓት ሲሆን «አዳም ብቻውን የሆን ዘንድ አይገባውም የምትመቸውን እረዳት እንፈጠርለት» ብሎ ወዲያውኑ በአዳም እንቅልፍ አመጣበት ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወስዶ ለአዳም ምትረዳውን ሴት ፈጠረለት ዘፍ.2፣18-23 ኩፋ.4፣4። እግዚአብሔር ሔዋንን ከጎኑ ፈጥሮ ባሳየው ጊዜ አዳም «ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት ሥጋዋም ከስጋዬ የተገኘች ናትና ሴት ትባል» አለ (ዘፍ.2፣23)። ሕይዋን ማለት የሕያዋን ሁል እናት ማለት ነው፡፡ ዘፍ.3፣20 ሕይዋን ከጎኑ መፈጠሯ ወንድና ሴት (ባልና ሚስት) አንድ አካል መሆናቸውና የሰው ዘር ሁሉ ከአንድ ግንድ መገኘቱን ያመለክታል፡፡ ሔዋንን ስለ ሦስት ነገር ፈጥሮታል፦

  1. ረዳት እንድትሆን
  2. ዘር ለመተካት
  3. ከፍትወት ለመጠበቅ

ሰው ከፍጥረታት ሁሉ የከበረ ነው፡፡ (መዝ.48 ፣12) ይኸውም የሚታወቀው፦

  1. ፍጥረታት ሁሉ ከተፈጠሩ በኋላ በመፈጠሩ
  2. በእግዚአብሔር አራያና አምሳል በመፈጠሩ
  3. በምድር ላይ የሚኖሩ ፍጥረታት በሙሉ ገዥ አዛዥ ሆኖ በመፈጠሩ
  4. የእግዚአብሔር የእጁ ፍጥረት በመሆኑ ( በገቢር የተፈጠረ ) ብቸኛ ፍጥረት በመሆኑ።

22ቱ ሥነ-ፍጥረት የሚባሉት እነዚህ ከላይ ያየናቸው ናቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ቅዳሜ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ከስራው አረፈ፡፡ ስለዚህ ይህች ዕለት ሰንበት ሆና እንድትከበር ሥጋዊ ስራዎች እነዳይሰሩባት የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሆነ፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ከስራው ሁሉ አርፎባታልና ነው /ዘፍ.2፣2/፡፡

ሥነ ፍጥረት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

አምላካችን አሏህ ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠረ፦ 50፥38 ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

"ፊ" فِي ማለት "ውስጥ" ማለት ሲሆን በጥቅል ስድስት ቀናት ውስጥ ሰማያትን እና ምድርን እንደፈጠረ ጉልኅ ማሳያ ነው፦ 7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

"በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ፊ" فِي የሚለው መስተዋድድ በጥቅል አገላለጽ ፍጥረት በስድስት ቀናት ውስጥ መፈጠራቸውን አመላካች ነው። በተናጥል ሌላ አንቀጽ ላይ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ መፍጠሩትን ይናገራል፦ 41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን?" ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ሁለት ቀናት" የተባሉት የመጀመሪያው ቀን "አል አሐድ" ٱلْأحَد እና ሁለተኛው ቀን "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن‎ እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦

ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥9 "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው" ሲል "የመጀመሪያው ቀን እና ሁለተኛው ቀን ነው" ማለት ነው"። فقوله : ( خلق الأرض في يومين ) يعني : يوم الأحد ويوم الاثنين .

፨ "አሐድ" أحَد ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን "እሑድ" ማለት ነው፥ "እሑድ" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ “አሐደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ" ማለት ነው። ፨ "ኢስነይን" اِثْنَيْن‎ ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን "ሰኞ" ማለት ነው፥ "ሰኞ" ማለት "ሰነየ" ማለትም "ደገመ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ሁለተኛ" ማለት ነው። አሏህ በምድር ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፦ 42፥10 በእርሷ ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا

"ባረከ" بَٰرَكَ ማለት "ባረከ" ማለት ሲሆን በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦ 42፥10 "በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ"፡፡ وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ

"በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ" አለ እንጂ "በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ፈጠረ" አላለም፥ "ወሰነ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" በሚል ይመጣል፦ 80፥19 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው እና መጠነው፡፡ مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ 25፥2 ነገሩንም ሁሉ የፈጠረ እና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" ለሚለው የገባው ቃል ግን "ቀደረ" قَدَّرَ ነው፥ በአራት ቀናት የመጠነው እና ያዘጋጀው ምግቧን እንጂ ፈጠረ አይልም። ምድርን የፈጠረበት 2 ቀናት እና ምግቧን የወሰነበትን 4 ቀናት ደምራችሁ 6 ቀናት ብላችሁ ለማጋጨት የሞከራችሁት ሙከራ ፉርሽ ሆኗል።

ሲጀመር "ተዳኹል" تَدَاخُل የሚለው ቃል "ተዳኸለ" تَدَاخَلَ ማለትም "ተጠላለፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጠላለፍ"intersection" ማለት ነው፥ አራት ቀናት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተዳኹል የሆኑት "አል አሐድ" ٱلْأحَد "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن‎ "አል ሱላሳእ" ٱلْثُّلَاثَاء "አል አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ናቸው፦ ተፍሢሩል ጀላለይን 41፥10 "በአራት ሙሉ ቀናት በሌላ አነጋገር በውስጧ ያለው የተራሮች አቀማመጥ ከሥስተኛው እና ከአራተኛው ቀን ጋር ተያይዞ የተከናወነው በትክክል "ሠዋእ" በተሳቢ ምክንያቱም ግሣዊ ስም ነው፥ አራቱ ቀናት ያነሱም ያልበዙም ለጠያቂዎች ሁሉ ስለ ምድር አፈጣጠር እና በውስጧ ስላለው ሁሉ በትክክል አራት ነበሩ"።

"ሠዋእ" سَوَآء ማለት "በትክክል" ማለት ሲሆን በሰዋስው አወቃቀር አራት ቀናት በሁለት ቀናት ውስጥ ተለጣጥፎ"overlap" የመጣ ነው። ፨ "ሱላሳእ" ثُّلَاثَاء ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ማክሰኞ" ማለት ነው። "ማክሰኞ" ማለት "ማግስት" ማለት ነው፥ የእሁድ ማግስት "ሦስተኛ" ቀን ነው። ፨ "አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ማለት "አራት" ማለት ሲሆን "ረቡዕ" ማለት ነው፥ "ረቡዕ" ማለት "ረበዓ" ከሚል የመጣ ሲሆን "አራተኛ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ሰማይን ጋዝ አርጎ ፈጠራት፥ ሰማይ የተገነባችበት ጋዝ ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣውን ጋዝ ነበረ፦ 79፥27 ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አሏህ ገነባት፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 42፥11 እርሱ(ጋዙ) ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣው ጭስ ነው"። وهو : بخار الماء المتصاعد منه حين خلقت الأرض

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَان ሲሆን “ጋዝ”gas" ማለት ነው፥ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አሏህ ለሰማይ እና ለምድር፦ «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦ 42፥11 "ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

ሰማይን ከፈጠረ በኃላ በሁለት ቀን የፈጠራትን ምድርን የእንቁላል ቅርጽ አርጎ ዘረጋት፥ "ዘረጋ" እንጂ "ፈጠረ" አይልም። "ዘረጋ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ደሓ" دَحَا ሲሆን የስም መደቡ "አድ ደሕያ” الدِّحْيَّة ነው፦ 79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

"ከዚህ በኋላ" ማለት ከሰማይ መፈጠር በኃላ ማለት ነው። "አድ ደሕያ” الدِّحْيَّة ማለት “የሰጎን እንቁላል” ማለት ሲሆን አሏህ ምድርን “የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረጋት” የሚል ትርጉም አለው። ፦ Dr. Kamal Omar Translation ፦ Ali Unal Translation ፦ Shabbir Ahmed Translation፦ “የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረጋት”He made the earth egg-shaped”

ብለው ተርጉመውታል። አሏህ ምድርን እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርጽ አርጎ ያደላደላት ለእኛ ስለሆነ "ለእናንተ" በማለት ይናገራል፦ 55፥10 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ وَالْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ 71፥19 አላህም ምድርን “ለእናንተ” ምንጣፍ አደረጋት፡፡ وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا 2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا አሏህ ምድርን እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርጽ አርጎ አደላድሎ በምድር ያለውን ማዕድናት፣ እጽዋት እና እንስሳት ለእኛ ፈጠረ፥ "በምድር ያለውን ሁሉ" የሚለው ማዕድናትን፣ እጽዋትን እና እንስሳትን ያካትታል። ከዚያ በጭስ መልክ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አርጎ ጨረሳት አስተካከላት፦ 41፥12 በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት "አደረጋቸው"፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ 2፥29 ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፥ ሰባት ሰማያትም "አደረጋቸው"፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

"ወደ ሰማይ አሰበ" "ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ" ማለቱ በራሱ ሰማይ በጋዝ ደረጃ ተፈጥራ እንደነበረ ጉልህ ማሳያ ነው፥ "ከዚያም" ማለት ምድር እና ምድር ላይ ያለውን ከፈጠረ በኃላ ማለት ነው። አሁንም 41፥12 ላይ "አደረገ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዷ" قَضَىٰ ሲሆን "ጨረሰ" በሚል ይመጣል፦ 27፥29 ሙሳም ጊዜውን በ-"ጨረሰ" እና ከቤተሰቦቹ ጋር በኼደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ፡፡ فَلَمَّا قَضَىٰ مُوسَى الْأَجَلَ وَسَارَ بِأَهْلِهِ آنَسَ مِن جَانِبِ الطُّورِ نَارًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጨረሰ" ለሚለው የገባው "ቀዷ" قَضَىٰ እንደሆነ በአጽንዖት ልብ አድርግ በተጨማሪ 2፥29 ላይ "አደረገ" ለሚለው የገባው ቃል "ሠዋ" سَوَّىٰ ሲሆን "አስተካከለ" በሚል ይመጣል፦ 87፥2 የዚያን ሁሉን ነገር የፈጠረውን እና ያስተካከለውን፡፡ الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያስተካከለ" ለሚለው የገባው "ሠዋ" سَوَّىٰ እንደሆነ በአንክሮት ልብ አድርግ ስለዚህ ምድር እንደ ሰጎን እንቁላል ከመደላደሏ በፊት የፈጠራትን ጭሳዊ ሰማይ ሰባት ሰማያት አርጎ ፈጸማት አስተካከላት። "ቀዷሁነ" قَضَىٰهُنَّ "ሠዋሁነ" سَوَّىٰهُنَّ በሚል መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለው "ሁነ" هُنَّ የሚለው ሦስተኛ አንስታይ መደብ "ሂየ" ‏هِيَ ለሚለው ብዜት ነው፥ "ሂየ" ‏هِيَ ማለት "እርሷ" ማለት ሲሆን "ሠማእ" سَّمَآء የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሰማይን ሰባት ሰማያት አድርጎ የጨረሰው እና ያስተካከለው በሁለት ቀናት ውስጥ ነው፥ እነዚህ "ሁለት ቀኖች" የተባሉት አምስተኛው ቀን "አል ኸሚሥ" ٱلْخَمِيس እና ስድስተኛው ቀን "አል ጁሙዓህ" ٱلْجُمُعَة እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥12 "በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው" ከዚያ ፈጽሞ በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት አስተካከላቸው፥ ሌላው ሁለቱ ቀናት አምስተኛው ቀን እና ስድስተኛው ቀን ናቸው። ( فقضاهن سبع سموات في يومين ) أي : ففرغ من تسويتهن سبع سموات في يومين ، أي : آخرين ، وهما يوم الخميس ويوم الجمعة .

፨ "ኸሚሥ" خَمِيس ማለት "አምስት" ማለት ሲሆን "ሐሙስ" ማለት ነው፥ "ሐሙስ" ማለት "አምሽት" "አምስት" ማለት ነው። ፨ "ጁሙዓህ" جُمُعَة ማለት "ስብስብ" ማለት ሲሆን "ዓርብ" ማለት ነው፥ "ዓርብ" የሚለው "ረበዐ" ማለትም "ሰበሰበ" ማለት ሲሆን "መሰብሰቢያ" "ስድስተኛ" ማለት ነው። አሏህ ለመላእክት፦ "እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ፥ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ" ብሎ በነገራቸው መሠረት ሰውን በስድስተኛው ቀን ፈጠረ፦ 38፥71 ጌታህ ለመላእክት «እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ 2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ! وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 1 አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ فِيهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ

ለመሆኑ ባይብል ላይ ፈጣሪ ሰማይን እና ምድርን የፈጠረው በየትኛው ቀን ነው ይላል? ዘፍጥረት በመጀመርያው ቀን ይለናል፦ ዘፍጥረት 1፥1 በመጀመሪያ ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን ፈጠረ። בְּרֵאשִׁ֖ית בָּרָ֣א אֱלֹהִ֑ים אֵ֥ת הַשָּׁמַ֖יִם וְאֵ֥ת הָאָֽרֶץ׃ ዘፍጥረት 1፥5 ኤሎሂምም ብርሃኑን "ቀን" ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት፡ አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን። וַיִּקְרָ֨א אֱלֹהִ֤ים לָאֹור֙ יֹ֔ום וְלַחֹ֖שֶׁךְ קָ֣רָא לָ֑יְלָה וַֽיְהִי־עֶ֥רֶב וַֽיְהִי־בֹ֖קֶר יֹ֥ום אֶחָֽד׃ פ

"ዮም" י֥וֹם ማለት በነጠላ "ቀን" ማለት ሲሆን ይህ የመጀመሪያ ቀን ስለሆነ "አንድ" ለሚለው "ኤኻድ" אֶחָֽד በማለት ይነግረናል። ዘጸአት ደግሞ በስድስት ቀናት ይለናል፦ ዘጸአት 31፥17 ያህዌህ ሰማይን እና ምድርን በስድስት ቀናት ፈጠረ። כִּי־שֵׁ֣שֶׁת יָמִ֗ים עָשָׂ֤ה יְהוָה֙ אֶת־הַשָּׁמַ֣יִם וְאֶת־הָאָ֔רֶץ

"ያሚም" יָמִ֗ים ማለት "ቀናት" ማለት ሲሆን "ዮም" י֥וֹם ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "ሼሼት" שֵׁ֣שֶׁת ማለት "ስድስት" ማለት ነው። ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን የፈጠረው በስድስት ቀናት ወይም በመጀመርያው ቀን? ይህ በቀላሉ ከመለሳችሁት የቁርኣኑ ነጥብ መረዳት ትችላላችሁ። አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

reference

[2] [3] [4] [5] [6] [7] [8]

  1. ዘካ.1፣9-13 ሉቃ.1፣19
  2. ሰማኒያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ
  3. ሥርወ ሃይማኖት
  4. ፍሬ ሃይማኖት
  5. መርሐ ጽድቅ ባሕለ ሃይማኖት
  6. ኮክሃ ሃይማኖት
  7. አምደ ሃይማኖት
  8. መዝገበ ሃይማኖት
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.