ማርክሲስም-ሌኒኒስም
ማርክሲስም-ሌኒኒስም በተለይ በካርል ማርክስና በቭላዲሚር ሌኒን ትምህርት የተመሠረተ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነው።
ማርክሲስም-ሌኒኒስም የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና በመሆኑ፣ በሃይማኖት ፈንታ እንደ የመንግሥት ሃይማኖት ያህል ያለ ሚና አጫውቷል።
በአሁኑ ሰዓት በይፋ የማርክሲስት-ሌኒኒስት መንግሥት ያላቸው አገራት የሚከተሉ ናቸው፦
- ቬትናም - ከ1937 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1982 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «የሆ ቺ ሚን ሃሣብ» ተብሏል።
- የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ - ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1970 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «ሶሻሊስም ከቻይናዊ ጸባይ ጋራ» ተብሏል።
- ኩባ - ከ1951 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።
- ላዎስ - ከ1967 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።
- ስሜን ኮርያ - ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ በይፋ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1964 ዓም ጀምሮ ከማርክሲስም የተደረጀው ርዕዮተ ዓለም «ጁቼ» ኰሙኒስም ተብሏል። በ1983 ዓም ደግሞ «ማርክሲስም» በይፋ ተተወ።
ርስት ሁሉ የመንግሥት መሆኑ እንጂ የግል ርስት አለመኖሩ የሚገኝበት ሁናቴ የጀርመን ፋላስፋ የካርል ማርክስ ፍልስፍና ውጤት ነው። በተጨማሪ ማርክስ የሃይማኖት ወዳጅ ባለመሆኑ መጠን፣ ባለፈው ጊዜ በማርክሲስም-ሌኒኒስም በተገዙት አያሌ አገራት ውስጥ የሃይማኖት ወይም የኅሊና ነጻነት አልተገኘም።
በካርል ማርክስም ፍልስፍና ዘንድ ማንም ሕዝብ እንዳይበልጽጉ መቆጣጠር የመንግሥት ኃላፊነት ነው፣ ስለዚህ «ለሴ ፈር» ከ«ካፒታሊዝም» ጽንሰ ሀሣብ ጋር ይዘመዳል።
በቻይና
ቻይና ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን ርዕዮተ አለሙ በይፋ «የማው ፀ-ቶንግ ሃሣብ» (ማዊስም) ነበር። በ1970 ዓም ወደ «ሶሻሊዝም ከቻይናዊ ጸባይ ጋር» ተቀየረ። በተጨማሪ «ሕዝብ እንዳይበልጽጉ» የሚለውን የማርክስ ጽንሰ ሀሣብ ትተዋል። የቻይና መሪ ደንግ ሥያውፒንግ በ1976 ዓም እንዳለ፣ «ሶሻሊስም ማለት ደህነትን ማጥፋት ማለት ነው።»
ስሜን ኮርያ
ባለፈው ጊዜ
የካርል ማርክስና የሌኒን ርዕዮተ ዓለም ቀድሞ ባለፈው ክፍለ ዘመን በበርካታ አገራት ተስፋፍቶ ነበር። ይህም ሁልጊዜ በአብዮትና በብሔራዊ ጦርነት ነበር።
- የሶቭየት ኅብረት - (1910-1984 ዓም)
- ሞንጎሊያ - (1917-1984 ዓም)
- ዩጎስላቪያ - (1936-1984 ዓም)
- ፖላንድ - (1937-1982 ዓም)
- አልባኒያ - (1937-1984 ዓም)
- ቡልጋሪያ - (1939-1983 ዓም)
- ቼኮስሎቫኪያ - (1940-1982 ዓም)
- ሮማንያ - (1940-1982 ዓም)
- ሀንጋሪ - (1941-1982 ዓም)
- ምሥራቅ ጀርመን - (1942-1983 ዓም)
- ደቡብ የመን - (1960-1982 ዓም)
- ኮንጎ ሪፐብሊክ - (1960-1984 ዓም)
- ሶማሊያ - (1962-1983 ዓም) (* የሶማሊያ ርዕዮተ ዓለም ማርክሲስም ከእስልምና ጋር ተቀላቀለ እንጂ እንደ ሌሎቹ ሁሉ ከሃዲነትን አልተቀበለም።)
- ኢትዮጵያ - (1966-1983 ዓም)
- ካምቦዲያ - (1967-1981 ዓም)
- ሞዛምቢክ - (1967-1983 ዓም)
- ቤኒን - (1968-1982 ዓም)
- አንጎላ - (1968-1984 ዓም)
- አፍጋኒስታን - (1970-1984 ዓም)
- ግረነይዳ - (1971-1976 ዓም)
በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በደርግ ዘመን (1966-1983 ዓም) በይፋ ማርክሲስት-ሌኒኒስት / ኰሙኒስት ነበረ።
የኢሕአዴግ መንግሥት (1983-2012 ዓም) ይፋዊ ርዕዮተ ዓለም «አብዮታዊ ዴሞክራሲ» ደግሞ በከፊል ከማርክሲስም-ሌኒኒስም የተደረጀ ሲሆን አንዳንድ የማርክስና በተለይም የሌኒን ተጽእኖዎች ቀርተው ነበር፤ ነገር ግን ከ1983 ዓም ጀምሮ በይፋ ርዕዮተ አለሙ ማርክሲስም / ኰሙኒስም አልነበረም። ከ2012 ዓም ጀምሮ ግን የአሁኑ መንግሥት ርዕዮተ አለም ለብልጽግና መደመር ነው።
[[መደብ:ሶሺያሊዝም