ማሪ

ማሪመስጴጦምያ ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ሐሪሪ ተብሎ ብዙ ጽላቶች የተገኙበት ፍርስራሹ በዘመናዊው አገር ሶርያ ውስጥ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይገኛል።

ማሪ
(ተል-ሐሪሪ)
የማሪ ፍርስራሽ
ሥፍራ
ማሪ is located in Syria
{{{alt}}}
ዘመን 2350-1673 ዓክልበ.
ዘመናዊ አገር ሶርያ
ጥንታዊ አገር ማርቱ

የማሪ ነገሥታት

ከማሪ ጽላቶች እንዲሁም ከኤብላ ጽላቶች ከተገኘው በርካታ መረጃ የማሪ ነገሥታት ዘመኖች ሊታወቅ ይቻላል።

መጀመርያ የሚታወቀው የማሪ ንጉሥ በኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ዘመን (2345-2314 ዓክልበ. ግ.) የነገሠው ጋንሱድ ይመስላል። ጋንሱድ ከመስ-አኔ-ፓዳ ጋር በዚህ ዘመን ንግድ እንዳካሄደው ይታወቃል። ከዚያ በኋላ የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ግዛቱን እስከ ማሪ ድረስ አስፋፋ። በኤአናቱም መሞት (2195 ዓክልበ. ግ.) ማሪ እንደገና ነጻ መንግሥት ሆነ።

  • ኢኩን-ሳማሽ 2195 ዓክልበ. ግ.
  • ኢኩን-ሳማጋን
  • ላምጊ-ማሪ (ኢሽኪ-ማሪ)
  • አኑቡ
  • ሳዑሙ
  • ኢቱፕ-ኢሻር
  • ኢብሉል-ኢል 2127?-2115 ዓክልበ. ግድም - «የማሪና የአሹር ንጉሥ» ተባለ፤ ከርሱ በኋላ ግን አሦር ነጻ ሆነ።
  • ኒዚ 2115-2114 ዓክልበ. ግድም
  • ኤና-ዳጋን 2114-2112 ዓክልበ. ግድም - የኤብላ ንጉሥ ኢሻር-ዳሙ የሾመ አለቃ ነበረ።
  • ኢኩን-ኢሻር 2112 ዓክልበ. ግድም
  • ሒዳዓር 2112-2077 ዓክልበ. ግድም - ከ2107-2100 ዓክልበ. ግ. ደግሞ የሱመር (ኒፑር) ንጉሥ እንደ ሆነ ይመስላል።
  • ኢሽቂ-ማሪ 2077-2068 ዓክልበ. ግድም

አካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ማሪን ያጠፋው በኢሽቂ-ማሪ ፱ኛው ዓመት ይመስላል። ከዚያ በአካድ መንግሥት ዘመን አለቃው ኢዲዲሽ በማሪ ላይ ተሾመ። ከእርሱ በታች «ሻካናኩ» (ሻለቆቹ) የተባለው ኟሪ ወገን በማሪ ተነሣ። እነርሱም፦

  • ሱ-ዳጋን 2068-2063
  • ኢሽማህ-ዳጋን 2063-2018
  • ኑር-መር 2018-2013
  • ኢሽዱብ-ኤል 2013-2002
  • ኢሽኩን-አዱ 2002-1994
  • አፒል-ኪን 1994-1959 - ከሰነዶች ዘመኑ የኡቱ-ኸጛልና የኡር-ናሙ ዘመናት እንደ ጠቀለለ ይረጋገጣል።
  • ኢዲን-ኢሉም 1959-1954
  • ኢሉም-ኢሻር 1954-1942
  • ቱራም-ዳጋን 1942-1922
  • ፑዙር-ኤሽታር 1922-1897 - የፑዙር-ኤሽታር ፩ኛው ዓመት የሹልጊ ፵፬ኛው ዓመት መሆኑን ይታወቃል።
  • ሒትላል-ኤራ 1897-1890
  • ሐኑን-ዳጋን 1890-1882
  • ኢሲ-ዳጋን 1882-1876?
  • ኢቱር-? 1876-1870 ?
  • አመር-ኑኑ 1870- 1864 ?
  • ቴር-ዳጋን 1864-1856 ?
  • ዳጋን-? 1856-1850 ?

...

  • ያጊት-ሊም ?-1723
  • ያኽዱን-ሊም 1720-1707
  • ሱሙ-ያማን 1707-1705
  • 1 ሻምሺ-አዳድ (በአሦር መንግሥት) 1705-1694
  • ያስማህ-አዳድ (1694-1687)
  • ዝምሪ-ሊም 1687-1673

በ1673 ዓክልበ. ማሪ ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ወደቀ።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.