ሚያዝያ ፴

ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ።

ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። [1]
  • ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው።
  • ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ።
  • ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። [2]

ልደቶች

ማጣቀሻዎች

  1. መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)፣ገጽ ፻፵፰
  2. (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/190144 Ethiopia: Annual Review for 1965
  3. (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 Ethiopia: Annual Review for 1974

ዋቢ ምንጮች


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.