ሚያዝያ ፳፫

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፫ኛው ዕለት ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፻፴፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፻፴፪ ዕለታት ይቀራሉ።

ሚያዝያ ፳፫

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሞተበትን ዕለት ማስታወሻ አድርጋ ትዘክረዋለች፡

“በዘአዕረፈ እግዚእየ ማር ጊዮርጊስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዘተከለለ ወርኁ በጽርዕ ጵንፍልዮ ስሙ ዘበትርጓሜሁ ሚያዝያ አመ ፳ወ፫ ለሠርቅ ወዕለቱሂ ዓርብ በጊዜ ፱ቱ ሰዓት አሜን።”

“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ጌታዬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረፈበት ሰማዕትነቱን የፈጸመበት ወሩ በጽርዕ ጵንፍልዮ ይባላል። ይኸውም ሚያዝያ ነው ወሩ በባተ በሃያ ሦስት ቀን ዕለቱም ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ነው አሜን።” [1]

ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፯፻፺፭ ዓ/ም - የአሜሪካ ኅብረት መንግሥት የኦርሊአንስ ግዛት የተባለውን ክፍል ከፈረንሳይ ላይ በ አሥራ አምስት ሚሊዮን ዶላር ገዛ።
  • ፲፰፻፬ ዓ/ም ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከፈረንሳይ የተገዛው የኦርሊአንስ ግዛት ሉዊዚያና ተብሎ የአሜሪካ አሥራ ስምንተኛው የኅብረት አባል ሆነ።

ዕለተ ሞት


ዋቢ ምንጮች

  1. ገድለ ጊዮርጊስ፦ በግእዝና በአማርኛ፣ ፲፱፻፺ ዓ/ም፣ ገጽ ፻፶፰-፻፶፱


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.