ሚያዝያ ፬

ሚያዝያ ፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፩ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የመጀመሪያውን ጠፈርተኛ፣ የ፳፯ ዓመት የአየር ኃይል ዓባሉን ዩሪ ጋጋሪንን በመኖራኩር ተኮሰች። ጋጋሪን ከባቢ አየርን ሰንጥቆ፣ በኅዋ ምድርን ለአንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ያህል ከዞረ በኋላ ወደመሬት ተመልሷል።
  • ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የአሜሪካ የበረራ እና የጠፈር አስተዳደር ድርጅት (NASA) ‘ስፔስ ሻትል’ በመባል የሚታወቀውን አየር ዠበብ/የጠፈር መንኮራኩር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደጠፈር ተኮሰ። ይኽ የመጀመሪያው አየር ዠበበ/መንኮራኩር ‘ኮለምቢያ’ (Columbia) የተባለው ሲሆን ሃያ ሰባት ጊዜ ወደጠፈር ተተኩሶ ከተመለሰ በኋላ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ/ም ተመልሶ ወደምድር ሲገባ ተቃጥሎ ተሰባበረ።

ልደት


ዕለተ ሞት


ዋቢ ምንጮች


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.