ሚያዝያ ፫

ሚያዝያ ፫፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፪ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች


  • ፲፰፻፷ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በ ሎርድ ናፒዬር የሚመራው የእንግሊዝ ሠራዊት እና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በመቅደላ ተራራ ሥር በምትገኘው እሮጌ በምትባል ሥፍራ ላይ ጦርነት ገጥመው የዓፄ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገብርዬ ሞቱ።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤት ጭቆና ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሰብዓዊ መብት ሕግ አጽድቀው ፈረሙ።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ ስለ ጋራ ጉዳዮች ለመወያየት የሰሜን አፍሪቃ አገሮችን መጎብኘት ጀመሩ።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በታንዛኒያ መንግሥት ድጋፍ የተንቀሳቀሱ የኡጋንዳ ታጋዮች የአገሪቱን በትረ-ሥልጣን ከአምባ ገነኑ ኢዲ አሚን እጅ ፈልቅቀው ጨበጡ። አሚን ሸሽቶ ወደሊቢያ ኮበለለ።

ልደት


ዕለተ ሞት

  • ፲፰፻፷ ዓ/ም - የዓፄ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገብርዬ ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በተደረግ ውጊያ እሮጌ ላይ ሞቱ።

ዋቢ ምንጮች


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.