መጋቢት ፳፱
መጋቢት ፳፱፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፱ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፮ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሥሩ የሚተዳደር ዓለም አቀፍ የሕዝብ ጤንነት ባለ ሥልጣን ድርጅት - ‘የዓለም ጤንነት ድርጅት’ን ( The World Health Organization (WHO)) መሠረተ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በርዋንዳ በጎሳ ልዩነት ላይ የተመሠረተው የእርስ በእርስ ፍጅት፣ የሁቱ ጎሠኞች እስከ ፰ መቶ ሺ የሚሆኑ የቱትሲ ብሔር ተወላጆችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ ፈጇቸው። የውጭ መንግሥታትን በጉዳዩ ጣልቃ እንዳይገቡ በተጤነ ዕቅድ፣ የርዋንዳ ሠራዊት በዚሁ ዕለት አሥር የቤልጂግ ጸጥታ አስከባሪ ወታደሮችን ገድለዋል።
ልደት
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.